ኤች አይ ቪ/ኤድስ በመከላከልና በመቆጣጠር ተግባር የማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍን ትግበራን ማስረፅ የላቀ ሚና እንዳለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ከሚዲያ አካላት ጋር በጋራ ለመምከር ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መደረክ ላይ መገለፁ ታውቋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በንግግራቸው የኤችአይቪ ስርጭቱን በመግታት ሀገራችን እ.ኤ.አ. በ2030 ላቀደችው ከኤድስ ነጻ የሆነች ሀገር መደላድል ይፈጥራ የተባለለት የማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍ ግንዛቤን ማስፋት ተጠባቂ ነው ብለዋል ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖችን፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና እና የተዋልዶ ጤናቸውን የመለወጥ አቅም ማጎልበት ሚያው ሚናውን ሊወጣይገባዋል ብለዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ /መንግስት ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሙኚዩኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀድራላህ አህመድ የኤች አይ ቪ /ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ግብ ጥሎ ተግባርን ከመፈጻምና ውጤትን ከማሻሻል አንጻር ለውጦች መኖራቸውን አመካክተው ለዚህም ሚዲያው የማይተካ ሚና ተጠቃሽ መሆኑን በማመላከት በቀጣይ ማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህሳቤን በማስረፅ የባህሪ ለውጥ ተግባራትን ለማጠናከር የሚዲያ አካላት ተሳትፎአቸው ከመቼውም ይልቅ ሊጎለብት እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡፡
ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ሁሉንም ማሕበረሰባዊ፣ መንግስታዊ፣ ሐይማኖታዊ እና የግል ተቋማትን በባለቤትነት ማሳተፍ የተገታ መተላለፍ ላይ ለመድረስ የተቀመጠውን ግብ በተግባር ማጀብ እንደሚገባ ተመላክቷል፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ