ለእናቶችና ህፃናት ጤና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚጠመዱ አመራሮች እና ባለሙያዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በመልዕክታቸው እንደ ክትባት ዘመቻ ያሉ ስራዎችንና ሌሎች የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን ለመቅረፍ የሚከናወኑ ተግባራትን ከመደገፍ ይልቅ በማደናቀፍ ለሌሎች ጥያቄዎቻቸው ማስያዣ ለመጠቀም የሚሞክሩ አካላት በየትኛውም ስሌት ትክክል ሊሆኑ እንደማይችሉ በመረዳት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አሳስበው በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አካላት የክልሉን ህዝብ ጤና ለማሻሻልና የህዝቡን ፍትሃዊ የጤና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያመች መልኩ በማህበረሰብ ደረጃ የተደራጁ አደረጃጀቶችን እንደገና አንቀሳቅሶ በመጠቀም ረገድ ትርጉም ያለው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።

በዛሬው ዕለት በየደረጃው ከሚገኙ አፈ-ጉባኤዎች እና ከማህበራዊ ዘርፍ ሴቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ በጉድለት ከተገመገሙ ጉዳዮች መካከል የህፃናት ሞት ለመከላከል የሚሰጡ የክትባት ዘመቻዎችን፣ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንን ለማጠናከር እንዲሁም በወረርሽኝ መልክ የተከሰቱ የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰሩ ተግባራትን በመደገፍ የተጣለባቸውን ሃላፊነት ከመወጣትና ለቆሙለት ህዝብ ከመወገን ይልቅ ጥያቄዬ ካልተመለሰ በሚል ሰበብ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያደናቅፉ አካላት ከእንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብና ድርጊት ሊቆጠቡ እንደሚገባ የምክር ቤት አባላቱ አሳስበው፦
በቀጣይ አስከፊው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ይበልጥ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ በዞንና በወረዳ ካለው የጤናና የትምህርት መዋቅር ጋር ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ።