ጋሞ ዞን 78 ሺህ 952 የማሕበረሰብ አካላትን ከወባ በሽታ መከላከል መቻሉ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።

ጋሞ ዞን 78 ሺህ 952 የማሕበረሰብ አካላትን ከወባ በሽታ መከላከል መቻሉ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ። የዞኑ ጤና መምሪያው ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታዬ ሕብረተሰቡን ከወባ በሽታ ለመጠበቅ ትኩረት ተሠጥቶ አየተሠራ ነው ብለዋል ። በተጠናቀቀው የሥራ ዘመን 147 ሺህ 744 ህዝብ በተሳተፈበት 57 ሺህ 252 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ጊዜያዊ የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል ። የመምሪያው ኃላፊ አንዳሉት በሠላም በር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁለት ወባማ ቀበሌያት 8ሺህ 600 በኬሚካል የተነከረ የአልጋ አጎበር በማሠራጨት 4028 ቤተሰብ ከወባ በሽታ መከላከል ተችሏል። የበሽታው ጫና በሚታይባቸው 63 ቀበሌያት ውስጥ በ10 ሺህ 573 መኖሪያ ቤቶች የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት በመካሄዱ 74 ሺህ 924 የማህበረሰብ ክፍሎችን ከበሽታው መታደግ ተችሏል ። በበጀት ዓመቱ በርካታ ሰዎች የተመላላሽ ህክምና ማግኘታቸውን የተናገሩት አቶ ወንድማገኝ ከተመላላሽ ተካሚዎች መካከል የደም ምርመራ እና የህመም ስሜት ልየታ ከተደረገባቸው 229 ሺህ 304 ሰዎች በ55 ሺህ 534 ታማሚዎች ላይ የወባ በሽታ ተገኝቶባቸው የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። በዘንድሮው በጀት ዓመትም የወባ በሽታ የሚያዙ ሰዎችን መጠን ከ100 ሰዎች መካከል አሁን ካለበት 32 ከመቶ ወደ 16 ከመቶ ለመቀነሰ ታቅዶ እየተሠራ ነው ። (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን):