የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ዞናዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በካራት ከተማ  በይፋ ተጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተግኝተው ንግግር ያደረጉት የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻው ኩሲያ እንዲሁም የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ እንግዳ ገለቦ እንዳሉት አካልን ለጉዳት አልፎም ለሞት የሚዳርገውን ተላላፊ የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በትኩረት ሊሰራና ህፃናትን ሊያስከትብ ይገባል ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አራርሶ ጋሮ እንደተናገሩት ዛሬ ከጥቅምት 12 ጀምሮ እስከ 15 ድረስ የሚቆይ መሆኑን አሳስበዋል።
መምሪያ ኃላፊው አቶ አራርሶ ጋሮ እንዳሉት በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና በ43 ቀበሌያት ለሚገኙ ከ53 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህጻናትን ለመከተብ 339 የህክምና ባለሙያዎችና ሌሎች አካላት ክትባቱን እነእደሚሰጡ አስታውቋል

የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ዋንኛው አማራጭ ክትባቱን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እድሜያቸው አምስት አመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ህጻናት ማስከተብ ስችሉ እንደሆነም መምሪያ ኃላፊው አስረድተዋል።

ዘመቻው በቀጣይ ወር ዳግም ሊሰጥ እንደሚችልም በመጠቆም።

ክትባቱ በሁሉም ቀበሌ ቤት ለቤት የሚሰጥ ሲሆን የኮሮና ጥንቃቄን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል ተብሏል።