የጤና ሚኒስቴር በ22ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በ22ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡ የተበረከተላቸውን ሽልማት በታላቅ ክብር ተቀብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ(ኮቪድ- 19) በጤና፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው ረገድ እያሳደረ የመጣው ጫና ለመካከል እንደ ክልል ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸው ተጠቃሽ ነው ፡፡ በመሆኑም በዚህ የላቀ ትግበራ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪውና የዞኑ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አብዱል ዋሪስ ጀማል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመካከል የተጉ የክልሉን ባለውለታዎች ሁሉ ያማከለ ሽልማት አግኝተዋል፡፡

ካበረከትዋቸው አስተዋፅዖዎች መካከል የመንግስት ሀብት ውስን በመሆኑ እንደ ዞኑ የህብረተሰቡን አቅም በማንቀሳቀስ ከ30 ሚሊዮን በላይ ብርና ሀብት እንዲሰበሰብ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል በመምራት እና በማስተባበር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡

በህዝብ መካከል ያለውን ፍቅር፣ አብሮነት፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ እና መከባበር እንደ ቁልፍ መሳሪያ በመጠቀም ከህብረተሰቡ ጋር ይበልጥ ተቀረባርቦ በመስራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ሚናቸው የጎላ ነው፡፡

በተባበረ ክንድ ችግሮቻችንን እንወጣለን በሚል መሪ ሃሳብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንትጋ መርሃቸው መነሻ በትጋት የማስተባበር ሚናቸው ይጠቀሳል ፦ይህም በክልል ደረጃ ጭምር ለተመዘገበው ውጤት ያበረከተው አስተዋጽ የላቀ ነው፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከአረፋ እና ፆም ፍቺ በዓላት ጋር ተያይዞ እንዳይስፋፋ በዓሉን ለማክበር ወረርሽኙ ከተስፋፋባቸው አከባቢዎች በተለይም ከአዲስ አበባ ወደ ዞኑ የሚመጡ በርካታ ተወላጆችን ወደ ኳራንቲን እንዲገቡ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ በማስቻል በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በመለየት ወደ ህክምና ማዕከል እንዲገቡ በማድረግ በዚህም አስፈላጊውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በማገዝ የተጫወቱት ሚና የላቀ ነው፡፡

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተበረከተው ሽልማት የደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ/ መንግስት ያደረገውን ዘርፈ ብዙ ጥረት ያገናዘበ በመሆኑ እንኳን ደስ አልዎ እንኳን ደስ አለን፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሞያቸው ኅብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ ያሉ አካላትን የማመስገንና እውቅና የመስጠት ተግባሩ እጅጉ ይበረታታል ።

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ