የጤና ልማት ስራዎችን አቀናጅቶ መምራት በዘርፉ ተጠባቂ የሆኑ ለውጦችን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተገለፀ

በጤናው ሴክተር በመደበኛና በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ቀርፎ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተግባራትን አቃጅቶ መምራት ቁልፍ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታውቋል፡
ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት ተጠባቂ ከሚያደርጓቸው ሁኔታዎች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም የሙቀት መጨመርን ተከትለው ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች በስጋትነት ይጠቀሳሉ ብሏቸዋል ፣
በማጅራት ገትር በሽታዎች የተጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር መጨመር፣ የኮሌራ ክስተት፣የተወሳሰበ የምግብ እጥረት፣ የወባ በሽታ ፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ክስተቶች የችግሮችን ስፋት እንደሚያጎላው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ የቅድመ ማስጠንቀቅና ማስገንዘብ በችግሩ ዙሪያ ምላሽ ሰጪ የአሠሣና ቅኝት ተግባራትን በማከናወን ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ብለዋል፡፡
በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ክስተቶች ሳቢያ በህብረተሰቡ ላይ የሚከሰትቱ ህመምና ከሞት መቀነስ ተግባራት ትኩረት ይሻሉ ይህ ህውን እንዲሆን ተግባርን አቀናጅቶ መምራት ይጠበቃል ነው ያሉት፡
በዚሁ ጊዜ ጊዜ የቀረቡ መረጃዎችን መነሻ ያደረጉና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችንም ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አመላክተዋል፡
በዘመቻ ከሚያዚያ መልክ ከሚያዚያ 7-10ቀን /2014 ዓ.ም ለተከታታይ 4 ቀናት ተደራሽ የሚደረገው ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት፣ የአየር ንብረት ለውጡን ተከትለው እተስተዋሉ ያሉ የጤና ችግሮችን ተዛማጅ መንስኤዎች በተለይም በከፋ የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን መለየትና ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡
ታክሞ መዳን በሚቻለው በፊስቱላ ህመም ምክንያት በየቤታቸው ተደብቀው የሚገኙ ሴቶች በሚደረገው የቤት ለቤት ለቤት ጉብኝት መለየትና ወደ ጤና ተቋም እንዲመጡ አንድም እናት ከበሽታው ጋር በተያያዘ ለሞት እንዳትዳረግ ማድረግ በዚህ ረገድ ተቀናጅተው በሚከናወኑ ተግባራት የህብረተሰቡን የንቃተ ጤና ማጎልበት የሚችሉ የጤና ተግባቦት ስራዎች በማጠናከር ተጠቃሽ ሆኗል፡፡
በመሆኑም በመደበኛውና በዘመቻ መልክ የሚከናኑ የጤና ልማት ስራዎች ውጤታማነት ባድርሻ አካላት አሳትፎ በህዝብ ንቅናቄ ተግባራት ጭምር መምራት በእጅ ያሉ አቅሞችን አማጦ የመጠቀም ባህል ሊጎለብት ይገባዋል ተብሏል፡፡