የደቡብና ሲዳማ ክልሎች በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ጤና ተቋማት የተደረገ ድጋፍ የደቡብ ኢትዮጵያና የሲዳማ ክልሎች የአማራ ክልል የጤና ተቋማትን ሊጠግኑ ነዉ የክልሎቹ የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ለዶቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት በአማራ ክልል የወደሙ የጤና ተቋማት የጉዳት ደረጃቸውን በመለየት በባለሙያና በቁሳቁስ አደራጅቶ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ። የደቡብና የሲዳማ ክልሎች በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት የወደሙ 35 የጤና ተቋማትን መልሶ የማደራጀት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ዐስታወቁ።።የየክልሎቹ የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ለዶቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት በአማራ ክልል የወደሙ የጤና ተቋማት የጉዳት ደረጃቸውን በመለየት በባለሙያና በቁሳቁስ አደራጅቶ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ድጋፉ እየተደረገለት የሚገኘው የአማራ ክልል የጤና ቢሮ የሥራ ኃ ላፊዎች በበኩላቸው ክልሎቹ የጀመሩት የድጋፍ እንቀስቃሴ በግጭቱ የደርሰውን ቁስል የሚጠግን ፣ የህዝቦችን ትሥሥር የሚያጠናክር ነው ሲሉ አወድሰዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዶቼቬሌ
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ