የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እንዳይከሰት እየተደረጉ ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች…

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እንዳይከሰት እየተደረጉ ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታውቌል መንኪፖክስ በተሰኘው ቫይረስ የሚከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው እ.አ.አ በ1958 ዓ.ም. ሁለት ለጥናት ያገለግሉ የነበሩ ዝንጀሮዎች በበሽታው ተጠቅተው በተገኙ ጊዜ ነበር አሁን ላይ በሽታው በምዕራብ አፍሪካ ዳግም ብቅ ብሏል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በበሽታው ከተጠቃ እንሰሳ ወይም ሰው ጋር በሚደረግ አካላዊ ንክኪ ይተላለፋል በሽታው ሲከሰት የሚከተሉትን አይነት ምልክቶች ትኩሳት ብርድ ፣ብርድ ማለት፣ራስ-ምታት ፣ድካም ፣የጡንቻ ህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም በበሽታው የተጠቃ ሰው በሚያስነጥስበት እና በሚያስልበት ጊዜ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፍ መቻሉ ተገቢውን ጥንቃቄ የሚሻ ተግባር ተደርጎ ይወሳል ፡ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ውይይቱን መርተውታል በመልዕክታቸውም ለዜጎች ጤና ቅድሚያ በመስጠት ለሚቀረጹ የጤና ፕሮግራሞች እና አስትራቴጂዎች በተገቢው እንደሚሰራባቸው በማመላከት ተለዋዋጭ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ተከትለው የሚከሰቱ የጤና ችግሮች በህብረተሰቡ ጤና ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመግታት ተከታታይነት ያለው የቅኝት እና አሰሳ ስራዎችን ማጠናከር ፣በመረጃ የተመሰረተ ውሳኔን ሰጭነትን የማጎልበት ተግባራትን ይጠይቃሉ ብለዋል፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እንዳይከሰት ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ማሳወቂያ እና ማስገንዘቢያ ተግባራት ትኩረት እንደሚቸራቸው በተመሳሳይ እየተስተዋለ ያከለውን የኩፍኝ ወረርሽኝ ለመግታት መደበኛ እና በዘመቻ የሚሰጡ የክትባት ተደራሽነትን ማሻሻል እንደሚገባም አስገንዝበዋል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬም የጤና ስጋት መሆኑ በዚህም የምርመራ ስራዎችን ማጠናከር ተግባራት ሊጠናከሩ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡