የዜጎች የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የጤና ኤክስቴንሽን መርሃግብርን ማጠናከር ይገባል

የዜጎች የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የጤና ኤክስቴንሽን መርሃግብርን ማጠናከር ይገባል – ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ
የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር የሚከናወኑ ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ ፡፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የተዘጋጀና በአገልግሎት አሰጣጥና መሰል ጉዳዮች የሚመክር ጉባዔ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ነው፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በዘላቂነት ለማረጋገጥ መንግስት ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው፡፡ ለዚህ አቅም እንዲሆን የማህበረሰቡን ጤና በምልዓት ለመጠበቅ የሚያግዝና መቀዛቀዝ ያሳየ የሚመስለው የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር መጠናከር እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ ህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ድርሻ የነበረዉ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም መቀዛቀዝ ማሳየቱን ገልጸው፤ ጉባዔዉ በትኩረት በመወያየት የጋራ ተልዕኮ መውሰድ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡