ወጣቱ ትውልድ ለኤች አይ ቪ/ኤድስ የሚኖረውን ተጋላጭነት ለመቀስ በሚያስችሉ ተግባራት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር ይገባል

 
መስከረም 13/2013ዓ.ም በጋማሊያ ሳይንሳዊ የምርምር ተቋም የተገኘው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት የቅደመ ምዝገባ ሙከራውን በሩሲያ እና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 42 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች እየተሰጠ ነው፤ ክትባቱን የወሰዱ ሁሉም ሰዎች ደግሞ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚችል አቅም መገንባታቸው ተረጋግጧል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ሩሲያ ‹‹ስቱትኒክ 5›› የሚል ስያሜ ስለሰጠችው እና የቅድመ ምዝገባ ሙከራ እየተደረገበት ስላለው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ያለውን አድናቆት ገልጧል፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ቀጣና ዳይሬክተር ሃንስ ክሉጌ ከሩሲያ የጤና ሚኒስትር ሚካኤል ሙራሽኮ ጋር ከነበራቸው ውይይት በኋላ ‹‹ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ክትባት ለመፍጠር ሩሲያ ላደረገችው ግሩም ጥረት አሁንም እንደገና ማመስገን እፈልጋለሁ›› ብለዋል፡፡
ክሉጌ እየተካሄዱ ያሉት የቅድመ ምዝገባ ሙከራዎች ስኬታማ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልፀው በሙከራው ለመሳተፍ የተስማሙ በጎ ፈቃደኞችን ሁሉ አመሥግነዋል፡፡ የክትባቱን ደኅንነት እና ውጤታማነት በበርካታ ሰዎች ላይ ለማረጋገጥ ሩሲያ ሦስተኛውን ደረጃ የክትባት ምርመራ ጀምራለች፡፡ ‹‹የእነዚህ ሙከራዎች ውጤት አዎንታዊ እንደሚሆኑም እርግጠኛ ነኝ፤ ሩሲያ በክትባት ልማት እጅግ የበለፀገ ታሪክ እንዳላትም አውቃለሁ›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ በተጨማሪም ሩሲያ ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ለመካከለኛው እስያ አገራት ዕርዳታ ለመስጠት ያደረገችውን ጥረት እና ለዓለም አቀፍ አንድነት ያላትን ቁርጠኝነት ዳይሬክተሩ አድንቀዋል፡፡ ሞስኮ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ብልቃት ክትባት ከ20 ሀገራት ጥያቄ ቢደርሳትም ባለሥልጣኖቿ ግን ሩሲያ ቅድሚያ ለዜጎቿ ልትደርስ ይገባል ብለዋል፡፡
ምንጭ (አብመድ)
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ