የዓለም ጤና ድርጅት ሦሥት በሙከራ ላይ የሚገኙ የኮቪድ 19 መድኃኒቶችን ይፋ አደረገ

የዓለም ጤና ድርጅት÷ በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ይቀንሳል ያላቸውን ሦሥት በሙከራ ላይ ያሉ መድኃኒቶች ይፋ አደረገ፡፡ በሙከራ ላይ ያሉት መድኃኒቶችም አርቴሱኔት፣ ኢሜቲኒብ እና ኢንፊሊክሲማብ እንደሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ መድኃኒቶቹ በቀጣይ በ 52 ሀገራት የኮቪድ 19 በሽተኞች ላይ ተሞክረው ውጤታማ ከሆኑ ጥቅም ላይ እንደሚውሉም ነው የተገለፀው፡፡
መድኃኒቶቹ አዲስ እንዳልሆኑና ሌሎች በሽታዎችን ለማከም ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ነው የተመለከተው፡፡
በዓለም ላይ እስካሁን በኮቪድ 19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ204 ነጥብ 28 ሚሊየን ሲልቅ በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ደግሞ ከ 4 ነጥብ 31 ሚሊየን በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ምንጭ ኤፋ ቢ ሲ
ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ