የክልሉ ጤና ቢሮ የ2012 በጀት ዓመት እና የ 2013 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓት ምግብ አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው

እናቶችና ህፃናት በቀላሉ መከላከል በሚቻልባቸው የጤና ችግሮች መሞት የለባቸውም መርዕን ትኩረት አድርጎ ተግባራትን በሚመራው በእናቶች እና ህፃናት ጤናና ስርሃተ ምግብ አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ ነው በመካሄድ ላይ ያለው።

በምክክር መድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ ሰራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት ፣የዞንና የልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤትና ጤና መምሪያ ሃላፊዎች ፣ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት ፣ የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች፣ ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል።

የእቅድ የአፈፃፀም እና የግምገማ መድረኩ በእናቶች ፣በህፃናት ጤና፣በቤተሰብ እና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች፣ በመረጃ ጥራት ትኩረቱን በማድረግ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ይመክርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፤የህፃናት የክትባት ሽፍን ችግር የማይታይበት ሆኖ በመደበኛ የጤና መረጃ እና በጥናት መረጃ መካከል ከፍተኛ ልዩነት እየታየበት መሆኑ በሚነሳው የክትባት አገልግሎት ደሰሳ ጥናት ሪፖርትም የውይይቱ አካል መሆኑንም በአጀንዳነት ተይዟል ።

በዚህ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ፣የተለዩ የአፈፃፀም ማነቆዎች ፣የመፍትሄ ሀሳቦች እና እስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ /መንግስት ጤና ቢሮ