የኤችአይቪ ስርጭትን ለመግታት የልየታና ህክምና ማስጀመር ተግባራትን ሊጠናከር ይገባል

ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም በቲቪ ልየታና ህክምና ማስጀመር ትኩረቱን ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በጉተራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ እንደሚገኝ የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ/መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል ።
ለኤች አይቪ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችና ደንበኞቻቸው ፣የተፋቱና የትዳር አጋሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ፣የቀን ወይንም የተንቀሳቃሽ ሰራተኞች፣የረጅም ርቀት ተጓዥ መኪና አሽከርካሪዎች ይጠቀሳሉ በመሆኑም እነዚህን ለይቶ ከመመርመርና ህክምና እንዲያገኙ ከማድረግ ረገድ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን መቅረፍ እንደሚገባ ተመላክቷል።
በኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች ልየታና ህክምና ማስጀመር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል በአፈፃፀም ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፉ ለተጋላጭ ተኮር የኤች አይ ቪ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች ልየታና ህክምና ማስጀመር ይህንንም ተግባር በንቅናቄው መፈፀም የመድረኩ አላማ መሆኑን የገለፁት የደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዘርፉ የሚጠበቀውን ግብ ለማሳካት በተለይም እ.ኤ አ በ2030 ኤችአይቪ /ኤድስ የህብረተሰብ የጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ዕውን ለማድረግ ፣የአመራሩ ሚና ፣የባለሙያዎች ርብርብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ ሊተካ የማይችል ሚና እንዳለው ተናግረዋል ።
በንቅናቄ መድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ የስራ አላፊዎች ፣የዞን ጤና መምሪያና ጤና ፅ/ቤት ሃላፊዎች ፣ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ማህበራት ፣የጤና ተቋማት አላፊዎች ፣የዘርፈ ብዙ ኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ፣የበሽታ መከላከል ባለሙያዎች ፣እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል።
የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት ጤናቸው ቢሮ