የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ስድስት ሆስፒታሎች…

ከክልላችን ተመርጠው በአገር አቀፍ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ስድስት ሆስፒታሎች 15 ሚሊዮን ብር ፣ ሜዳሊያና ሰርተፊኬት እንዲሁም ለአንድ ሆስፒታል ደግሞ የሰርተፊኬት ሽልማት ተበረከተላቸው

ይህ የ3ኛው ዙር የሆስፒታሎች የሽልማት መርሃ-ግብር በዋናነት የጤና ተቋማትን ፅዱና ምቹ በማድረግ እንድሁም ወቅቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት በመስጠት ተቋማዊ ለዉጥ በማስመዝገብ ረገድ የተሻለ ዉጤት ያስመዘገቡ ሆስፒታሎች ለሽልማቱ የተመረጡ መሆናቸውን ዶክተር ሊያ አክለው ገልጸዋል።

ለሽልማቱ የደረሱ 44 ሆስፒታሎች ሲሆኑ በየክልሎቹ በተቀመጠው የትኩረት አቅጠጫ መሰረት መስፈርቶችን አሟልተው የተመረጡ መሆናቸውን በጤና ሚኒስቴር የሜድካል ሰርቭስ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ያዕቆብ ሰማ ተናግረዋል።

ከ1ኛ-10ኛ ደረጃ የያዙት ሆስፒታሎች በአንደኛ ደረጃ ያጠናቀቁ ሲሆን የ 3 ሚሊዮን ብር ፤ የሜዳሊያ እና ሰርትፍኬት ተሸላሚዎች ሆነዋል። ከ11-35ኛ ያሉ በ2ኛ ደረጃ ያጠናቀቁ እና ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ሜዳልያና ሴርተፊከት የተሸለሙ ሲሆን ከ36ኛ-44ኛ ያሉ ደግሞ በ3ኛ ደረጃ በመያዝ ሰርተፊኬት አግኝተዋል። በዚህም ወራቤ ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2013 ሻምፒዮን ለመሆን ችሏል።

በቀጣይ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የትኩረት አቅጣጫ መረጃን መሠረት ያደረገ ተቋማዊ ለዉጥ ማምጣት እና ተገልጋይ ተኮር አገልግሎቶችን መስጠት መሆኑን ዶክተር ሊያ ገልፀዋል።

በዚህ መሠረት ከክልላችን ሻምፒዮኑን ወራቤ ኮምፕረኸንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ ቦንጋ ገ/ጻዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ንግስት ኢሌኒ መታሰቢያ ኮምረኸንሲቭ ሆስፒታል ከ1ኛ፣ 8ኛና – 9ኛ ደረጃ በማግኘታቸው እያንዳንዳቸው 3 ሚሊዮን ብር፣ ሜዳሊያ እና ሰርተፊኬት ሽልማት እና ቡታጅራ አጠ. ሆስፒታል 11ኛ፣ ጃንካ አጠ. ሆስፒታል 15ኛ እና አርባምንጭ አጠ. ሆስፒታል እያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን ብር፣ ሜዳሊያና ሰርተፊኬት ያገኙ በመሆናቸው በድምሩ 15 ሚሊየን ብር ማምጣት ችለዋል ። በተጨማሪም የሀላባ አጠ. ሆስፒታል እና ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል በመስፈርቱ መሠረት ባመጡት ውጤት የሰርተፊኬት ሽልማት ማግኘት ችለዋል።

ስለሆነም ለስራው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሙሉ እና መላው ህብረተሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አለን።