የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ተቋማዊ ለዉጥን ለማምጣት አጋዥ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቌል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ስድስት ሆስፒታሎች የገንዘብ ፣ የሜዳሊያ የሰርተፊኬት ሽልማት አስመልክቶ መልዕክት ተላልፎበታል።

የ3ኛው ዙር የሆስፒታሎች የሽልማት መርሃ-ግብር በዋናነት የጤና ተቋማትን ፅዱና ምቹ በማድረግ እንዲሁም ወቅቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት በመስጠት ተቋማዊ ለዉጥ በማስመዝገብ ረገድ የተሻለ ዉጤት ያስመዘገቡ ሆስፒታሎች በመስፈርቱ መሰረት አሸናፊ መሆናቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንደገለጹት ይህ እውቅናና ሽልማት በጋራ ርብርብ የመጣ ውጤት መሆኑን በመግለፅ ትልቁ ሽልማት ህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻል ነው ብለዋል፡፡

ቢሮው የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ በበኩላቸው በቀጣይ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የትኩረት አቅጣጫ መረጃን መሠረት ያደረገ ተቋማዊ ለዉጥ ማምጣት እና ተገልጋይ ተኮር አገልግሎቶችን በማስፋት ይበልጥ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚራና መሰል ማበረታቻዎችና ጥረትን የሚያጎለብቱ እውቅዎች ወደ ክልሉ በዘላቂነት እንዲመጡ የበለጠ ተግተን እንሰራለን በማለት ሽልማቱ ትልቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል ፡፡

የጋራ ጥረት ውጤትን ለማመላከት በቀጣይ ተግባብቶና ተቀናጅቶ ስራን መስራት ለድል እንደሚያበቃ ለማመልከት በተዘጋጀው የእንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቌል፡፡