የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በደ/ብ/ብ/ህ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ተከበረ

የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገንባ” በሚል መሪ ለ45ተኛ ጊዜ ዛሬ በደ/ብ/ብ/ህ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ተከበረ በመድረኩ የተገኙት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናዉ ካዉዛ “የሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ነው በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ የሚገኘው የሴቶች ቀን በታሪካዊነቱ የሚነሳ መሆኑን በማንሳት በሁሉም መስክ የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግበራት ቢከናወኑም በተለየ መልኩ ተጠቃሽ የሆኑ ተግዳሮቶችም መስተዋላቸውን አውስተው በቀጣይም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሴቶችን የእኩልትና የፍትሃዊነት ችግሮችን ለመፍታት እንቅስቃሴ የተጀመረበት እና ሁለንተናዊ ትግል የተጀመረበት፤ ይህንንም እንቅስቃሴና ውጤት ለመዘከር ሲባል ዕለቱ በየዓመቱ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከበርና ልዩና ታሪካዊ ቀን ለመሆን መብቃቱን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወሰን ግዛቸው በመልዕክታቸው አስገንዝበዋል።

በበአሉ ላይ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ ስራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተግኝተዋል በመድረኩም የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚከሰተውን የማህፀን በርጫፍ ካንሰር ምንነት እንዲሁም የመከለከያ መንገዶችን በተመለከተ ወይይት ተድርጓል፡፡ ህጻናት ማቆያ መቋቋሙም ተነግሯል፡፡ ይህም ህጻናት ማቆያ በማቋቋም እናቶች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ እንደሚያግዛቸው እንዲሁም በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ የተደረገው የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብሩ በጤናው ሴክተር የተቀመጡ የግብ ስኬቶችን በጋራ እውን ለማድረግ የተሻለ ሥራ ለመስራት የሚያበረታታ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ I am Generation Equality: Realizing Women’s Rights በሚል መሪቃል እንዲሁም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ”የሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ የሚገኘው የሴቶች ቀን በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ረገድ ያለው ዓስተዋጽኦ በማድረግ ረገድ ትልቁን ሚና ይጫወታልም ብለዋል፡፡