የቲቢ ተዛማችነትን መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት አፅንዖት ሊሰጥባቸው እንደሚገባ ተገለፀ

ዕድሜን፣ ፆታን፣ ዘርንና ቀለምን ሳይለይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነው፤ከተስፋፋባቸው ቀዳሚ የዓለም ሀገራት ውስጥ ኢትዮዽያ ትገኝበታለች በየቀኑ 400 ሰዎችን ለሕመም ፣ 59 ሰዎችን ለሞት እየዳረገም ይገኛል የቲቢ በሽታ፦

በቲቢ እና በመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ምክንያት በአለም ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለኢኮኖሚያዊ፣ ለማህበራዊ እና ለሌሎች ዉስብስብ ችግሮች እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ በመሆናቸው በርካታ ተግባራት ሊሰሩ ይገባቸዋል፡፡

ይህንንም ህውን ለማድረግ የቲቢ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቲቢ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች መለየት በጤና ምርመራ እንዲያገኙ ማድረግ እነዚህን በማህበረሰቡ ውስጥ የበሽታውን ስርጭት ፈልጎ ማግኘት ና አክሞ ማዳን የቲቢ ተዛማችነት ቁጥጥር መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት እየተሰራባቸው መሆኑን የተናገሩት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሌ ማቴ በቲቢ እና ከመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ራሳችንና ሌሎችን ለመጠበቅ በሥራ ቦታ፣ በሕዝብ መጓጓዣ እና በቤት ውስጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ለሚዲያና ለኮሙኒዩኬሽ ባለሙያዎች በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የቲቢ ጉዳይ የአመራሩን፤ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማጠናከር ቀጣይነት ያለው የማስገንዘብና የማሳወቅ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባቸው ተመላክቷል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ ጤና ጤና ቢሮ