ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ቁልፍ የሆነውን የሰርአተ ምግብን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላትን አሳታፊ ያደረጉ ተግባራት …

በምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች የህፃናትን መቀንጨር በ2000 ከነበረበት ከ58 በመቶ በ2019 ወደ 38.6 በመቶ መቀነስ የተቻለ ሲሆን የመክሳት ችግርን ደግሞ በ2000 ከ41 በመቶ በ2019 ወደ 21.1 በመቶ እንዲቀንስ ለማድረግ መቻሉን መረጃዎች ይጠቁማሉ ፦
በዚህ ረገድ ያሉ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የባህሪ ለውጥ ተኮር ስራዎችን ማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በዞኖችና በልዩ ወረዳዎች ከሚገኙ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር የጋራ ውይይት ተደርጓል ።

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መ ንግስት ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፍዬ ሌጅሶ በአንድ ሀገር ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ሲታሰብ ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራትን ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ለዚህም ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረጉ የማስተማር ፣የማሳቅ ስራዎችን ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተንግረዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀድራህ አህመድ በበኩላቸው በአህምሮ የዳበረና የበለፀገ ትውልድን ለማፍራት ስርዓተ ምግብን ማጠናከር ፍይዳው የጎላ በመሆኑ ተግባር ተኮርና ትክክለኛ መረጃ በመጠቀም የተግባቦት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በውይይት መድረኩ የምግብ አለመመጣጠን ችግር ፣የፕላምፕሌት አለአግባብ መጠቀም ፣በ (የኮቪድ -19) መካከለና መቆጣጠር የህፃናት የአመጋገብ
የሚሉ የመወያያ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ፦

በዚህም ከዞኖችና ከልዩ ወረዳዎች ከመጡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች አንዳንንዶች በሰጡት አስተያየት ፦የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናትን ጤናቸው ተጠብቆ በተገቢው እንዲያድጉ የስርዓተ ምግብ ችግሮችን መቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ተገቢውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ሂደት የመረጃ እጥረት ፣ቅንጅታዊ አሰራር ፣ በተለይም ከህገ ወጥ መድሃኒት ንግድ ረገድ ቁጥጥር ስርዓት ወጥነት ያለው የተጠያቂነትና አሰራርን በተግባር መረጋገጥ ፤ተገቢ መሆኑን አመላክተው ከውይይቱ መነሻ የሚጠበቅባቸውን አስተዎፅዖ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።