የቀጣይ የ15 ዓመታት የጤና ኤክስቴንሽን ፎኖተ ካርታን በተግባር ማጀብ በጤናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥን ለመረጋገጥ ያስችላል

አስፈላጊ የሆኑ የጤና ማለትም የመከላከል፣ የማበልፀግ፣ የፈውስ፣ የተሃድሶና የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶችን አስተማማኝ በሆነ መንገድ በተግባር ለማረጋገጥ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ማጠናከር ሚናው የላቀ መሆኑ በተለያዩ ጊዜያትና ሁኔታዎች ይገለፃል ።

አዋጪ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ውጤታማና የሀገራችን መለያ የሆነ ፕሮግራም በአሁኑ ጊዜ የሚጠበቅበትን ያህል ውጤት እያስመዘገበ አይደለም ይሄንንም ለመቅረፍ ስትራቴጂውን ከወትሮው በተለየ መንገድ በመከለስ እውን ማድረግ እንደሚያሻ ተመክሮበታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተለዩ ውስንነቶችና ተግዳሮቶች ለፕሮግራሙ መቀዛቀዝ የሚፈለግበት ግብ እያስመዘገበ አሰንዳይቀጥል አድርገውታል ። ከዚህም ባሻገር ለፍኖተ ካርታው መከለስ በምክንያትነት የተለዩ ሐሳቦችም ተካተዋል ፦

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአካል ጉዳቶች እየጨመሩ መምጣታቸው፤ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፓኬጆች ለህብረተሰቡ የጤና ፍላጎቶች ጠቃሚ ቢሆኑም ሁሉ አቀፍነት የሚጎድላቸው ሆነው መገኘታቸው የመርሀ ግብሩን ክለሳው ይበልጥ አንገብጋቢ አድርገውታል ።

በትምህርት ቤቶች፣ የወጣት ማዕከላት፣ ተቋማትና የሥራ ቦታዎች በፕሮግራሙ ላይ የስራ ጫና እና ዕድሎችንም መፍጠሩ፤ የመጣውን ልጆች፣ ወጣቶች እና ጎልማሳዎች በአገልግሎት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆንና በቀጣይም እነዚህንና መሰል የጤና አጀንዳ ግቦችን ዕውን ለማድረግ የቀጣይ 15 ዓመት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታን ይፍ ማድረግ ማስፈለጉ ተመልክቷል ።