የምግብና ስርዓተ ምግብ ፖሊሲን ማረጋገጥ ጤናማ ትውልድ መፍጠር እንደሚረዳ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቌል፡ የምግብና ስርዓተ ምግብ ፖሊሲዉ በቀጣይ የሰዉ ልጅ ሰብአዊና ህገ መንግስታዊ መብት የሆነዉን የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር እዉን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ቀጣይ ሀገር ተረካቢ ትዉልድን የማፍራት ዓላማን ፣በነፍሰ ጡር እናቶች፣ ጡት በሚጠቡ ሕፃናት ላይ ተገቢዉን ትኩረት በማድረግ በአካልም በአእምሮም የዳበረና የበለፀገ ትዉልድ እንዲፈጠር ምግብና ስርዓተ ምግብን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገነሞ ወልዴ በመልዕክታቸው ስርዓተ ምግብ ለህፃናት እድገት፣ ለአካላቸው መዳበርና ለአዕምሯቸው ጤናማ አስተሳሰብና እድገት እጅግ ወሳኝ መሆኑንና ለእናቶችም በእርግዝና ወቅትም ሆነ ወልደው በሚያጠቡበት ጊዜ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።ህፃናት በአካላዊና በአዕምሯቸው የመቀንጨር ችግር እንዳይገጥማቸው በርካታ ስራዎች መከናወናቸውንም አቶ ገነሞ አያይዘው ገልፀዋል። የጤና ፅ/ቤቱ ባለሙያዎችም በባቲ ሌጀኖ ቀበሌ ጤና ኬላ ግቢ በመገኘት እናቶች በአከባቢያቸው ባሉ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬና አትክልት የመሳሰሉ የስርዓተ ምግብ አዘገጀጀትና አጠባበቅ ዙሪያ ለልጆች፣ ለነፍሰ ጡር እናቶችና ለሚያጠቡ እናቶች በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫና ስልጠና ነክ ትምህርቶችን ሰጥተዋል። በዚህም ስልጠና ለእናቶች በምግብ አዘገጃጀት እንዳለባቸውና ጤናቸውን እንዴት በምግብ መጠበቅ እንዳለባቸውና ልጆቻቸውን እንዴት መመገብ እንዳለባቸው የሚያስችል ስልጠናም ተሰጥቷቸዋል። ሰልጣኝ እናቶች በሰጡት አስተያየትም በኋላ በቤታቸው በሚገኝ ግብዓት ለልጆቻቸው ትኩረት በመስጠት ክትትል እንደሚያደርጉና በአካልና በአእምሮ የዳበረ ቤተሰብ እንዲኖራቸውም ከጤና ባለሙያዎች በተሰጣቸው ስልጠና መሰረት በስርዓተ ምግብ አጠባበቅና አዘገጃጀት ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ በመፍጠር ለቀጣይ ትምህርትምልምድ መቅሰማቸውንም ገልፀዋል።
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ