የማሕበረሰብ አቀፍ የጤና መድሕን አገልግሎትን በማጠናከር ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ 9ኛ ጊዜ “ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው ለተወለዱ ህጻናት የወላጅ ዕቅፍ ፍቱን ህክምና ነው በሚል መሪቃል“ ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው የተወለዱ ህጻናት ቀን እየተከበረ እንደሚገኝ የደ/ብ/ብ/ህ /ክ/መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በየዓመቱ በዓለም ላይ ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ጨቅላ ህፃናት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑት የአንድ ወር ዕድሜ ሳይሞላቸው ይሞታሉ።
በኢትዮጵያ ደግሞ 376,700 የሚወለዱ ሲሆን 27,600 የሚሆኑት የአንድ ወር ዕድሜ ሳይሞላቸው ለሞት መዳረጋቸው የችግሩን አሳሳቢነት ያጎላዋል፡፡ የደ/ብ/ብ/ህ /ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ ጨቅላ ህፃናት ከ 37ኛው የእርግዝና ሳምንት በፊት ሲወለዱ ከመወለጃ ቀናቸው በፊት እንደተወለዱ ይቆጠራል ይህም በመሆኑ ጨቅላ ሕጻናት ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው በመወለዳቸው የተለያየ የጤና እክሎች እንደሚገጥማቸው ይገልፃሉ ። ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው የሚወለዱ ጨቅላ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከዚህ ክስተት ጋር ተያይዞ የሚከሰተው መጠነ ሞት ከ 5 ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት መጠነ ሞት ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል፡፡ በመሆኑም የመወለጃ ቀን ሳይደርስ ለሚከሰት ውልደት ተገቢው ትኩረት በመስጠት ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት ልዩ እንክባካቤ መስጠት እንደሚገባ ገልጸው ወጪ እና የገላ ለገላ ንክኪ እንዲሁም የወላጅ ዕቅፍ በራሱ ፍቱን ህክምና መሆኑን ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ለህብረተሰቡና ለወላጆች ግንዛቤ ለመፍጠር ተግባራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው በሚወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ላይ የሚደርሰውን ህመም፤የአካል ጉዳት እና ሞት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ የዓለም ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው የሚወለዱ ሕፃናት ቀን መከበር መልካም አጋጣሚን ከመፍጠሩም በላይ ሊደረግ በሚገባው ምላሽ ላይ ለመወያየት ዕድል ይፈጥራል፡ በመሆኑም የመሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስ ጠንክረን የምንሰራበት የህፃናት ጤና አገልግሎት ውጤታማነትን ለማስቀጠል በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።
ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው ለተወለዱ ጨቅላ ህጻናት አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ክብካቤ በመስጠት ዙርያ የወላጆቻቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ረገድ ተንከባክበው ያሳደጉ ሕጻናት ወላጆች የካንጋሮ “ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው ለተወለዱ ህጻናት የወላጅ ዕቅፍ ፍቱን ህክምና ነው!! መርዕን በተግባር አሳይተዋል የህይወት ምስክርነታቸውንም ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ /ክ/መንግስት ጤና ቢሮ