የሕብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ

መምሪያው የ2013 በጀት አመት ተግባር አፈፃፀም ማጠቃለያ በመገምገም በተሻለ ለፈፀሙ ወረዳዎች፣ ከተሞችና ተቋማት ዕውቅና በመስጠት እና መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የውይይት መድረኩ በ2014 በጀት ዓመት የጤናው ሴክተር ዋና ዋና ግቦችን በተሻለ በመፈፀም ህዝቦችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መሆኑም ታውቋል፡፡ በተግባር አፈፃፀሙ የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ዉጤት መነሻ በማድረግ የወረዳ የትራንስፎርሜሽን እና የመረጃ አብዮት መልሶ የማረጋገጥ ሥራ ትኩረት እንደተሰጠው ተመላክቷል፡፡ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነዉ አይዛ በንግግራቸው በዞኑ በ2013 በጀት ዓመት በታቀደዉ እቅድ መነሻ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መቆየታቸውን ገልፀው ይህንን አፈፃፀም በአገራዊ ስታንዳርድ መሠረት በመለካት እያንዳንዱ ወረዳ፣ ከተማና ጤና ተቋማት የደረሱበትን ደረጃ የመለየት ስራ መካተተቱን ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የፈፀሙትና ሳያሳኩ የቀሩ ተግባራት በመለየት ድርጊት መርሃ ግብር ታግዞ መስራት የቀጣይ ዓመት ተግባርን በተሻለ መፈፀም እንደሚያስችል በሁሉም ደረጃ ጤናማ የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ለመልሶ ማረጋገጫ ሥራ ተመድበው የሚሄዱ ባለሙያዎች የታቸኛውን መዋቅር ከመደገፍና ከማብቃት ረገድ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። በመጨረሻም በኦሬንቴሽን መድረኩ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ዉይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ያለው የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ነው፡፡