የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታን መከላከል ይቻላል!!

ህጻናትን የፖሊዮ ክትባት በማስከተብ የልጅነት ልምሻ በሽታን መከላከል ይቻላል
ፖሊዮ ቫይረስ ህፃናትን ለህመም ለሞት እና ለዘላቂ አካል ጉዳተኝነት የሚያዳርግ ተላላፊ በሽታ ነው ይሁን እንጂ ህፃናት ከልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታ ነጻ ሆነው እንዲያድጉ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታ መከላከያ ክትባትን ማስከተብ ይጠበቃል፡፡
የጤና ፖሊሲን በመትግበር በተሰራው ሰፊ ስራ መካከል ፖሊዮ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማጥፋት የተሠራው ስራ ይጠቀሳል። ይሁን እንጂ የፖሊዮ ዝሪያ በአንዳንድ አከባቢዎች እየተከሰተ በማምጣቱ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታ መከላከያ ክትባት መስጠት አስፈልጓል፡
ዛሬም በዓለማችን ባሉት ሃገራት የሚኖሩ አብዛኛዎቹ ሀገራት ክትባት ሙሉ በሙሉ የሚገባቸውን ያህል ሕፃናት ህይወት አድን የክትባት አይነቶች ማግኘት ባለመቻላቸው ለችግር ሲጋለጡ ይስተዋላሉ ።
እነዚህንና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ሁሉም አካባቢዎች ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ዕድሜቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባት ከሚያዚያ 7-10/2014 ዓ/ም ይሰጣል፡፡
“ህጻናትን የፖሊዮ ክትባትበ ማስከተብከ የልጅነት ልምሻ በሽታን እንከላከል!”
የፖሊዮ በሽታ ማለት ፖሊዮ በሚባል ቫይረስ ሳቢያ የሚከሰት የልጅነት ልምሻ በሽታ ነው። ይህ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው (ይልቁንም በልጆች መካከል) የሚተላለፍ በሽታ ነው።
የፖሊዮ ወርሽኝን ለመግታት ወይም ለማጥፋት በመደበኛ የክትባት ፕሮግራምና በዘመቻ መልክ በሚሰጡ ክትባቶች ህጻናቱ በሽታዉን የመከላከል አቅማቸዉን ለማጎልበት ከተወለዱ 1 ሰዓት ጀምሮ ያሉትን ህጻናት ጨምሮ እድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሁሉም ህፃናት ተደራሽ እንዲሆኑ መስራት አማራጭ የለውም ፡፡
ስለሆነ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ሚያዚያ 7-10 /2014 ዓ/ም በሚሰጠውን የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት ዘመቻ ልጆቻቸውን ማስከተብ ይኖርባቸዋል፡፡
የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታ በተለይ ህጻናትን ለአካል ጉዳት፣ ለህመምና ለሞት ከሚዳጉ በሽታዎች አንዱ በመሆኑና ይህንንም ለመከላከል ታላሚ ያደረገ ነው፡፡
“ህጻናትን የፖሊዮ ክትባት በማስከተብከ የልጅነት ልምሻ በሽታን እንከላከል!”
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ