ዕድሜያቸው  14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ መሳካት የጋራ ጥረት ውጤት ነው

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ አቶ ወንድሙ ዳንኤል በመልዕክታቸው ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (Human papilloma virus) የሚከሰተውን የማህፀን በር  ካንሰር መከለከያ ክትባት ዘመቻ  41,080 ልጃገረዶችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ይህም አጠቃላይ  አፈፃፀሙን 100%ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።

ዘመቻውን  ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማሳካት   ከጤናው ሴክተር  ባሻገር ከሌሎችም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ቅድመ ዝግጅት  መደረጉ እንዲሁም  የአመራሩ ቁርጠኝነትና ሚና ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዘመቻ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ ሲገባ ከትምህርት ተቋማት ውጪ የሚገኙ ታላሚዎችን ጭምር ተደራሽ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸው በአበረታችነቱ የሚጠቀስ ከመሆኑም ባሻገር  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አካቶ ለክትባት አገልግሎቱ ተደራሽነትና ጥራቱን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የጋራ እቅድ ከማዘጋጀት  ጀምሮ  ለተግባራዊነቱና ለውጤታማነቱ የጋራ ርብርብ  መደረጉንም  ያነሱት የከምባታ  ጠምባሮ ዞን ጤና  እናቶችና ህፃናት ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ  አቶ ማርቆስ  ጉርማሞ ናቸዉ ።

አቶ ማርቆስ አክለውም ይህ ዘመቻ ስኬታማ  እንዲሆን በዞን አስተዳዳር መሪነት የሁሉም መዋቅር አመራሮች ኃላፊነት እንዲወስድ በማድረግ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች  በዞኖች ፣ በሁሉም ወረዳዎች እና ከከተማ  አስተዳደሮች  ከሌሎች ጋር  በመቀናጀት እየሰሩ በመሆኑ  ለዘመቻው ስኬታማነት የግብረ_ሐይል ጠንካራ አሰራር የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት  ጤና ቢሮ