ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል በሚል መሪ ቃል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

 

ወባ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በአገራችንና በክልላችን ከፍተኛ የሆነ ህመምና ሞት ሲያስከትል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ወባን ለማጥፋትና ጤናማ የሆነ ህብረተሰብ እንዲኖር ለማስቻል ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ለውጦች መመዝገባቸው 2023 ዓ.ም ከወባ በሽታ ነፃ የሆነች ኢትዮጲያን ለማየት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የጋራ ርብርብና ጥረት እየተደረገም ይገኛል።

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሙኒዩኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀድረላህ አህመድ ከጥቅምት 1-7/2014 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የወባ ሳምንት አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው በወባ በሽታ ሳቢያ ሊደርስ የሚችለዉን ሕመምና ሞት ለማስወገድ የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ማገዝ የባለድርሻ አከላት ተሳትፎና ሚና ሊጎለብት እንደሚገባው በማስገዘብ “ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል” መርዕ ተግባራዊ ሃላፊነትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ የተነከረ አጐበር አቅርቦትና አጠቃቀም ፣ ፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ፣ ለወባ መራባት ምቹ የሚሆኑ ውኃ ያቆሩ ቦታዎች ማፋሳስና ማደፋን ሥራዎች ተጠባቂ ከመሆናቸው ባሻገር የወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና ተግባራትም ተጠባቂ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ሴክተሩ ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት በምርትና በምርታማነት፣ በማህበራዊና በጤናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተፅህኖ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ተግባራት የሚዲያ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸው በቀጣይም “ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል” መርዕ በተግባር ሊታጀብ እንደሚገባው አቶ ቀድረላህ አህመድ አስገንዝበዋል፡፡