ኮቪድ-19 በመደበኛ ጤና አገልግሎት ላይ እያስከተለ ያለውን ጫና ለመቀነስ ተግባራትን በጥምረት ይዞ መምራት ይገባል

ይህንኑ በተመለከተ ጉባሄው በመጀመሪያ ቀን ውሎው ትኩረት ሰጥቶ መክሮባቸዋል፦ በመሆኑም በሁለተኛው የጤናው ሴክተር የትራንስፎርሜሽ አጀንዳዎችን ለማሣካት ዘርፈብዙ ጥረቶ እየተደረጉ ቢሆንም በትኩረት አቅጣጫዎችን ከማሳካት ረገድ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።
የጋሞዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አስተዳዳሪ አቶ ተሻለ ማናዬ በመልዕክታቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጤና፣ በኢኮኖሚው ረገድ እያስከተለ ያለውን ጫና ተጠቃሽ ቢሆንም የተፈጠሩ እድሎችም የማይዘነጉ መሆናቸውን በማውሳት ተግባራትን በቅንጅት መተግበር ተገቢ መሆኑንም ገልፀዋል ።
የ/ደብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክቶሬት አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመቀነስ የተግባቦት ስራዎችን ፣መደበኛ የጤና አገልግሎት ስርዓቱን ማጠናከር፣ የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ከማስፍፍት ባሻገር ፣የምርመራ አቅምን ማሳደግ እንዲሁም ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተቀመጡ የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው በመፈፀም አላባቸው አስቸኳይ ግዜ አዋጆች መነሳት የቫይረሱ ስርጭት በዚህም ምክንያት የሚከሰት እህመምና ሞት መቀነስ ማለት ባለመሆኑ የአንዳችን ጥንቃቄ ለሁላችን መልዕክት አስተላፈዋል።
በዚሁ ግዜ ከተሳታፊዎች አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ቅድሚያ ለጤና ትኩረት ያሻዋል ፤በቀጣይ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል እንደ ግለሰብም ጭምር ልናሳካቸው ያለምናቸውን ግቦች ለማረጋገጥ የኮሮና ወረርሽኝን መከላከል ፣በለመዘናጋት ሁሉም እራሱንና ሌሎችን ከወረርሽኙ መከላከል ፤የተጀመሩ ተግባራትን ማስቀጠል ፤የሚስተዋሉ መዘናጋቶችን ለመቅረፍ የተቀመጡ መመሪያዎችን በመፈፀምና በማስፈፀም ሃፊነትን በተግባር መግለፅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል ።
ጉባሄው በሁለተኛ ቀን ውሎው በተነሱ አሳቦች ላይ መክሮ የጋራ አቅጣጫዎችን እንደሚያስ ቀምጥ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት እየቀረበ ባለው በእናቶች ጤና አገልግሎት ላይ በተመረጡ አከባቢዎች ላይ የተካሄደ ዳሰሳ ጥናት ምክረ አሳብ ይቀርብበታል ተብሎም ይጠበቃል ።