እጅን በመታጠብና በንፅህና መያዝ ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመቀነስ የግል ሃላፊነትን መወጣት ይገባል

በእለት ተእለት የተግባራት እንቅስቃሴ እጅን በመታጠብና በንፅህና መያዝ የግል ሃላፊነትን ለመወጣት ዓለም የእጅ መታጠብ ቀንን መነሻ ያደረገ ንቅናቄ የፖናል ውይይት በተደረገበት ወቅት መገለፁን የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የፕሮግራም ዘርፍ ሃላፊ አቶ መና መኩሪያ የዓለም እጅ መታጠብ ቀን ዓላማ ዋነኛ ትኩረቱ ዘላቂ ልማትን ለመረጋገጥ የህብረተሰቡ ጤና ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት በንቅናቄ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት መሆኑን በመግለፅ ፦

በዚህ ረገድ የጤና ኤክስቴሽንን መርሐ ግብር መነሻ በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ቢቻልም በህብረተሰቡ ዘንድ በሚፈለገው ልክ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ተብሎ መውሰድ አዳጋች በመሆኑን በማንሳት በቀጣይም ባለድርሻ አካላትን ፣ተፅህኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ፣ እንዲሁም የሚዲያ አካላትን ያሳተፈ ተግባራት ማጠናከር ዋና ተግባር ተደርጎ መፈፀም እንደሚገባው አመላክተዋል።

የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው እጆችን በውሃና በሳሙና በመታጠብ የኮሮና ቫይረስ ከመከላከልና መቆጣጠር ረገድ ከተቀመጡ አማራጮች መካከል ዋነኛው ከመሆኑ በሻገር በየዕለቱ በምናደርጋቸው ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ከእጆቻችን ንፅህና ጋር በእጅጉ የተቆራኙ በመሆናቸው በዚህ ረገድ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ፣ በማስተማርና ተሳትፎውን በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የባህሪ ለውጥ ትምህርት ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ይህንን መነሻ ያደረገ አስተያየት ተነስቷል፦ በዚህም ለመተግበር ቀላል ፤ ብዙ ወጪ የማይጠይቅና ኮሮናን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ለመከላከል የሚያስችለውን እጅ መታጠብ ተግባር ባህል አድርጎ ከመሄድ አንፃር ሰፊ ጉድለት መታየቱ በአሳሳቢነቱ እንደሚወሳ በማመላከት በቀጣይም በመደበኛው የጤና መርሃ ግብር ስራዎችን አቀናጅቶ መምራት የግል ንፅህና ግንዛቤ ስራዎች ለውጥ አምጪ በሆነ መልኩ መፈፀም እንደሚገባቸው ተገልጿል ።

በመጨረሻም ኮሌራን ጨምሮ በየወቅቱ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ የንፅህና ጉድለት በሽታዎችን ለማጥፋት ተቀናጅተን ተግባርን እንፈፅም መልዕክት በፓናል ውይይቱ በሰፊው ተመክሮበታል ።

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ /መንግስት ጤና ቢሮ