ኮቪድ19 የማህበረሰባችን ከፍተኛ የህልውና አደጋ መሆኑን ሁላችንም መረዳት ይኖርብናል

ኮቪድ የማህበረሰባችን ከፍተኛ የህልውና አደጋ መሆኑን ሁላችንም መረዳት ይኖርብናል፡፡ ከመቶ ሚሊየን በላይ የአለማችን ህዝብ አጥቅቶ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች ገድሎ የአለም ስጋት እንደሆነ ቀጥሎዋል፡፡ በሀገራችንም እስካሁን ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች መርምረን 154,257 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው 2,305 ሰዎች ህይወታቸው አጥተውበት አሁንም በየቀኑ በጣም አሰፈላጊ የሆኑ ሰዎች እያጣን ቤተሰብ እየተበተነ ይገኛል፡፡ ፊት ለፊት ሆነን የዚህን በሽታ ስርጭት እንዳይስፋፋ እና ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የምንሰራ ሰዎች እያጋጠመን ያለው ችግር እና በየቀኑ የምናሳልፈው በጣም አሳዛኝ ገጠመኞች ይህ በሽታ ምን ያክል ማህበረሰባችን እየጎዳ እንደሆነ በቃላት መግለጽ ይከብዳል፡፡ አሁንም በጣም ቀላል የሆኑትን መከላከያ መንገዶች በመተግበር ብዙ ህይወቶች ማትረፍ እንችላለን፡፡

– የአፍ እና የአፈንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሁልጊዜ በሁሉ ቦታ ማድረግ
– የእጅ ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ አለብን

ያዕቆብ ሰማን
(በጤና ሚኒሰቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር)