ኢትዮጲያ ታመሰግናችኋለች የጤና ባለሞያዎችና የጤና ክብካቤ ሰራተኞች የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር

ኢትዮጲያ ታመሰግናችኋለች የጤና ባለሞያዎችና የጤና ክብካቤ ሰራተኞች የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር በሀዲያ ዞን በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ መካሄዱን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ አስታውቋል::
በመድረኩ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የህለቱ የክብር እንግዳ አቶ እርስቱ ይርዳ ፣ የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ አጎ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የመንግስትና የግል ጤና አመራሮችና የባለሞያ ተወካዮች፣ባለድርሻ አካላት በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች የተሳተፉ ሲሆን በጤና ቢሮ የእውቅናና ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የህይወት ዋጋ በመክፈል ሲሰሩ ለነበሩ የጤና ባለሙያዎች እና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለህዝብ በመስጠት በተለይም በርካታ ችግሮችን ተቋቁመው በኮቪድ-19 ህክምና መከላከልና መቆጣጠር ላይ የተሰማሩ የጤናው ዘርፍ ባለሞያዎችና ሰራተኞች ህብረተሰቡን ስቃይና ህልፈተ ህይወት ለመታደግ ሙያቸውን እና የማይተካ ህይወታቸውን ጭምር ውለታ የማይረሳ ታሪካዊ በመሆኑ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ በኮቪድ- 19 ምክንያት ህይወታቸው ላለፉ የጤና ባለሞያዎችና ዜጎች የህሊና ፀሎት የጧፍ ማብራት የሀገርሽማግሌዎች ምረቃት ስነስርሃት በለባለሞያዎች የምስጋናና የጭብጨባ እንዲሁም የተለያዩ የጤና ባለሞያዎችን የሚዘክሩ ዶክመንተሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮግራሞች በሰፊው ቀርበዋል፡፡