አመታዊ ክልላዊ የጤና ጉባኤ ጥቅምት 13 ቀን ተጀምሯል

ጠንካራ የጤና ስርዓትን ማረጋገጥ በጤና ልማት አፈፃፀም የላቀ ዉጤትን ለማስጠበቅ እንደሚያስችል 2012 በጀት አመት የጤናው ሴክተር አፈጻፀምን በመገምገም በ2013 ዕቅድ ዝግጅት ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መገለጹን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ጉባሄው አጽንዖት ሰጥቶ ከሚመክርባቸው ጉዳዮች መካከል ፦የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጎልቶ የሚታዩ የፍታሃዊነትና ጥራት ያለው የጤና ጉድለቶች ላይ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ የአሰራር አቅጣጫዎችን ማመላከት ፣ አጠቃላይ የጤና ስርዓት ላይ የተጋረጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ(ኮቪድ-19) ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረጉ ጥረቶችና በሚወሰዱ እርምጃዎች በመምከር በአጠቃላይ ከጤናው ሴክተር አፈጻፀም ረገድ የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ስኬቶችን በጋራ አስጠብቆ ለመሄድ በሚያሥችሉ ጉዳዮች ላይ በሰፊው እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ቅድመ ክስተት ጥናት መርሃ ግብር በማስቀመጥ ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስረዓት በመዘርጋት የህብረተሰቡ የጤና ችግር ሆነው እንዳይቀጥሉ አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ተጠቃሽ መሆኑን በማንሳት በቀጣይም የአመራሩን ተሳትፎ በማጠናከር በወባ፣ ኮሌራ፣ የምግብ እጥረት እንዲሁም በሌሎችም የጤና ጉዳዮች በቀጣይ የአመራሩን ተሳትፎ በማጠናከር በርካታ ተግባራት መከናወን እንደሚገባቸው አመላክተዋል፡፡
በጉባሄው መክፈቻ የእናቶችና ህጻናት ጤና ላይ ፣በጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎ አሰጣጥ ፣በጤና ተቀማት ፍትሃዊና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ፣የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህንን በትኩረት ሊመራው ይገባል መልዕክት ተላልፏል፤
በ ዝቅተኛ አፈጻጸም ረገድ ዋና ጉድለት ተደርጎ የሚወሰደው የዓለም ዓቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ቢሆንም ከቦታ ቦታ ያለው የአመራር ቁረጠኝነት በማሻሻል፣ ተግባራትን በጥራት መፈፀም እንሚገባ ተመላክቶበታል፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚዘልቀውና በዛሬው ህለት በይፋ በተጀመረው በአፈጻፀም ግምገማውና በምክክር ጉባሄው ሃላፊዎች ፣የጤናው ሴክተር የልማት አጋር ድርጅቶች ፣የሥራ ሃላፊዎች ፣እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ መሆናቸው ተመልክቷል ።