ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎችን የመከላከል ተግባራት የአሳሳቢነቱን ያህል አለመሆኑን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ /መንግስት ጤና ቢሮ አስታወቀ

ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ አከባቢ በሽታዎች የሚባሉት ፣ትራኮማ፣ቢልሃርዚያ፣የአንጀት ጥገኛ ትላትል ፣ዝሆኔ በሽታዎች ይጠቀሳሉ የነዚህን በሽታዎች ጫና ለመግታት የሚከናወኑ ተግባራት ለውጥ አምጪ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ተግልጿል ።

ሀሩራማ ትኩረት የተነፈጋቸው በሽታዎች በጤና፣ በማህበራዊ ፣በኢኮኖሚው ረገድ የሚያሳድሩት ጫና የበረታ ቢሆንም የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች የበሽታውን አሳሳቢነት ያህል እንዳልሆኑ የተናገሩት የ/ደ/ብ/ብ/ህ /ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በቀጣይም ተግባራትን ከተለመደው አሰራርና ውጪ በመፈፀም በጋራ እንረባረብ ብለዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሌ ማቴ በበኩላቸው ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችለመከላከል፣ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሠራር ን ማረጋገጥ፤ ቅድሚያ ለህብረተሰቡን ጤና መርህን በተግባር ማጀብ ፍይዳው የጎላ መሆኑን በመጥቀስ በተለይም ትኩረት የሚሹ በሽታዎች ከሚያስከትሉትን ጫና ለመቀነስ ከመቼው ጊዜ በላይ መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በውይይት መድረኩ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ምንነት፣ የሚያስከትሉት ጫና፣የመከላከያ መንገዶችን እንዲሁም አሳሳቢ የህብረተሰቡ የጤና ችግሮች መሆናቸውን በተመከተ በቢሮው በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት የሀሩራማ በሽታዎች መከላከል ቴክኒካል አማካሪ በአቶ በላቸው ቦኪቾ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፦
በዚህም ወቅት የአካላ ጉዳትን ጨምሮ ለሞት የሚዳርጉ የሀሩራማ ትኩረት የተነፈጋቸው በሽታዎች የቅድመ መከላከል ስራዎች ሊተኮርባቸው እንደሚገባ በማመላከት ፤የበሽታዎቹን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ የአሰራር የመመሪያዎችን መጠቀም፣የአመራሩን ሚና ማጎልበት ፣የግንዛቤ ስራዎችን በጥምረት መስራት ፣የሚስተዋሉ የበጀት እጥረቶችን መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ