በፖሊዮ ህመም ምክንያት የሚከሰት የልጅነት ልምሻና ሞትን ለማስቆም ጥራት ያለው የክትባትን በትኩረት ማድረስ ይገባል

በፖሊዮ ህመም ምክንያት የሚከሰት የልጅነት ልምሻና ሞትን ለማስቆም በክልላችን በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች እድሜቸው 5 ከዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከጥቅምት 12/2014 ዓ/ም ጀምሮ በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ሄምቤቾ ቀበሌ እየተሰጠ ይገኛል::

የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት በመደበኛ የክትባት ፕሮግራምና በዘመቻ ህጻናቱ በሽታዉ የመከላከል አቅማቸዉን ለማጎልበት ከተወለዱ 1 ሰዓት ጀምሮ እድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሁሉም ህፃናት ተደራሽ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህ የክትባት ዘመቻ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተመልክተናል በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ከአምስት ዓመት በቻች ህፃናቶች ወረዳ ሂላማ 32,226 ሲሆን ክትባቱ በተካሄባቸው ሁለት ቀናት 19 ,930 ህጻናትን መከተብ መቻላቸውን ተናግረዋል በዚህም 61.8%ማሳካት መቻሉን የወረዳው አቶ ተፈራ ደጀኔ ተናግረዋል፡

በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ሄምቤቾ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት በለጠ እንዲሁም ወሮ አለሚጡ ጨንቆ የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ልጆቻቸውን በማስከብ መቻላቸውን ተናግረዋል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም በአከባቢው ቀስቃሾች ታግዘው መረጃ በማግኘታቸው ልጆቻቸውን ማስከተብ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ቀበሌ ክትባቱን ስታድርስ ያገኘናት የጤና ኤከክስቴንሽ ባለሙያ ወ/ሮ ወርቅ አለም ኀይሌ ለማህበረሰቡ መልዕክቱን በወቅቱ እና በጊዜው ተደራሽ በመደረጉ ክትባቱን እቤት ለቤት ያለ ምንም ንኪኪ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መስጠቷን ቀድሞ በተሰጣት አቅም ማጎልበቻ መሰረት የራሷን ጥንቃቄ ማድረጓን ገልጻ በትግበራ ወቅት የሚባል ችግር ባይገጥማትም ወቅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሰፊው የተስተዋለበት በመሆኑ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች የኮኖና ቫይረስ መከላከያ የጥንቃቄ መንገዶችን ማለትም እጅን በተደጋጋሚ በመታጠብ ፤ርቀትን በመጠበቅ፣አፍና አፍንጫን በመሸፈን ክትባቱን ከማስከተብ ረገድ ሰፊ መዘናጋቶች መስተዋላቸውን አመላክተዋል፡፡ በደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ