በጤናው ዘርፍ የተቋም ወሊድን በማጠናከር የእናቶችና ሕፃናትን ጉዳት መቀነስ እንደሚገባ ተገልጿል

በጤናው ዘርፍ የተቋም ወሊድን በማጠናከርና የእናቶችና ሕፃናትን ጉዳት መቀነስ እንደሚገባ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡ መምሪያው በከምባታ ጠምባሮ ዞን ስር በቀዲደ ጋሜላ ወረዳ የማህበረሰቡን የጤና ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተለይም የቅድመ ወሊድ ፣የወሊድና የድህረ ወሊድ እንዲሁም የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ በመስጠት ብቻ ሁለት ሶስተኛዉን ሞት መቀነስ እንደሚቻል መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የምንግስትን አቅጣጫና ፖሊሲ በተከተለ መልኩ በእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኘው መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት (ኬ ኤም ጂ)ን በማስተባበር በነፍሰ ጡር እናቶች ኮንፍራንስ 88 ነፍሰ ጡሮች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ለማበራታት ስጦታ አልባሳት አንሶላና ሳሙና አበርክቷል፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በሰቆጣ አዋጅ ስምምነት ትግበራ ላይ ለልማት ቡድኖች፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች፣ ለሚያጠቡ እናቶች እና ለተለያዩ አካላት በተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓት ላይ ሠርቶ ማሳያ ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት መከናወኑም ታውቋል፡፡
ምንጭ በከምባታ ጠምባሮ ዞን