በጤናው ሴክተር ተግባር ተኮር የመሪነት ሚናን በየደረጃው ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

በጤናው ሴክተር ተጠባቂ የሆነውን ለውጥ ለማስመዝገብ ተግባር ተኮር የመሪነት ሚናን በየደረጃው ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው የ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል።

የጤናውን ሴክተር የ5 ወራት እቅድ አፈፃፀም መገምገም ፣የጨቅላ ህፃናት ፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት ፣ ፣ማህበረሰብ ጤና መድህን ፣በክልሉ የኮቪድ _19 እና ሌሎች ወረርሽኞች ያሉበት ሁኔታ አዳዲስ የለውጥ አሰራሮችን በጋራ ለመቃኘት በዚህም ረገድ፦

የህብረተሰብን የጤና ሁኔታ ማሻሻል ግብ አድርጎ በሚዛን አማን ከተማ ለሁለት ቀናት ሲመክር የቆየው የ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ /መንግስት ጤና ቢሮ የጋራ የምክክር መድረክ ተጠናቋል ።

በውይይቱ ማጠናቀቂያ ወደ ኋላ የተመለሱ ዋናዋና የጤና ፕሮግራሞች አሳሳቢ ከመሆናቸው ባሻገር የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት የማይታሰብ ያደርገዋል ያሉት የደ/ብ/ብሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በውድቀት የተገመገሙ አፈፃፀሞችን አመላክተዋል ።

በመሆኑም የላቀ የመሪነት ሚናን በመወጣት በእናቶች እና ህፃናት ጤና፣ የወባ፣ ቲቢ፣ኤች .አይ ቪ. መከላከልና መቆጣጠር ፣የጨቅላ ህፃናት ሞትን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ሊመዘገብ እንደሚገባ አስረድተዋል ።

ተግባራትን ቆጥሮ ሰጥቶ በጠራ የመረጃ ስርሃት ቆጥሮ መቀበል ፣ቁርጠኛ የአመራር ስርሃትን ማጠናከር ፣ የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብርን ማጠናከር፣ ውጤታማ የሆነ የድጋፍ ክትትል ስራዎችን ማስቀጠል በቀጣይነት ያለው ውጤን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ሃላፊው በማጠቃለያቸው በፅንዖት ተናግረዋል ።

በውይይቱ ወቅት በቀጣይነት ከጤና ባለሙያዎች ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣ተገንብቶ በተገቢው አገልግሎት መስጠት ያልቻሉ ጤና ተቋማትን ማጠናከር እና በግብሃት ማሟላት ፣በየጊዜው ለሚከሰቱ ወረርሽኞች ፈጣን ምላሽ የመስጠት የተቋም ዝግጁነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥያቄዎች ቀርበው የከቤቱ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ።