በጤናው ሴክተር በጉድለት የተመዘገቡ አፈፃፀሞችን ማሻሻል ተጠባቂ መሆን ይገባዋል

በጤናው ሴክተር በጉድለት የተመዘገቡ አፈፃፀሞችን ማሻሻል ተጠባቂ መሆኑ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ አስታውቋል፡ ቢሮው የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ክንውን ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ውይይት ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤው የህጻናትን ህመምና ሞት ለመቀነስ በሚከወኑ ተግባራት በክትባት የምንከላከላቸው ወረርሽኞች መንሰራፋት በክትባት ፕሮግራማችን ላይ ከፍተኛ የጥራት ችግር መኖሩን አመላካች በመሆኑ በክትባት መድሃኒት አያያዝ ጋር የሚታዩ ጉድለቶችን በማረም፤የክትባት መርሃ ግብር ማሻሻል ይጠበቃል ብለዋቸዋል፡፡ 2014 በጀት ዓመት የስርዓተ-ምግብ ልየታ ማግኘት ከሚገባቸው እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ 2ሚሊዮን ህጻናት መካከል በአማካይ 1ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ በላይ (52%) ህጻናት ብቻ መሆኑን ከዚህ በተጨማሪ የስርዓተ-ምግብ ደረጃ ልየታ ስራ መደረግ ከሚገባቸው ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ እናቶች 54%ብቻ መሸፈን የተቻለ የመረጃ ምንጫችን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ የተሸሻለ መጸደጃ ቤት ግንባታ አፈጻጸም 55% ብቻ መሆን፣ የወባ በሽታ ክስተት ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲናጻጸር 41% ጭማሪ ያሳየ መሆኑ የአከባቢ ጥበቃ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥተዋቸው ባለመሰራታቸው እና ህብረተሰቡ የአልጋ አጎባር አጠቃቃም ጋር ያለው ጉድለት ተጠቃሽ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ቲቢን በመከላከል ተግባራት ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዘው የቲቢ ልየታ ተግባር ሲሆን በበጀት ዓመቱ ይኖራል ተብሎ ከሚገመተው ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች አገልግሎቱን ያገኙ ሲሆን ሽፋኑን 75% መድረስ ተችሏል፡፡ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ8% ዕድገት ያሳየ ቢሆንም ለዓመቱ ከተቀመጠው ግብ (85%) አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የአምቡላንስ አጠቃቀም ሥርዓታችንም ለእናቶቸና ለእናቶች አገልግሎት ብቻ እንደውል ማድረግ የህግ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚታዩ ፈጥኖ ማረም ይጠበቃል ብለዋቸዋል ፡፡
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ