የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን በመግታትና እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ በመቀነስ ትውልድን ማሻገር አፅንዖት ሊሰጠው ይገባል

የኤች አይ ቪ ስርጭትን በመግታት እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን በማጠናከር የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ማሻገር አማራጭ የሌለው ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ /መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል ።

ቢሮው ኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በጥምረት የተከናወኑ የዘርፈ ብዙ ምላሽ ስራዎች በጥንካሬ ሲገመግም በተለይም በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጭምር ፈታኝ የሆነው የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት ወቅት ቢሆንም በጥምረት የተከናወኑ የኤች አይ ቪ /ኤድስ መከላከል ተግባራት በጥንካሬ የሚጠቀሱ መሆናቸውን የ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የዘርፈ ብዙ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ተናግረዋል ።

የዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ /ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2012 ዓ.ም በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም ዕቅድ በጉድለት የተመለከታቸውን አፈፃፀሞች በመፈተሽ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክቷል በመሆኑም የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን በ2030 ለማስቆም የተያዘውን ግብ ስኬታማነትን ማረጋገጥ እንዳይቻል በጉድለት የሚነሱ ነጥቦች፦ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚደረጉ የማስተማርና የመቀስቀስ ስራዎች መቀዛቀዝ፣ የወጣቶችን ተጋላጭነት አለመቀነስ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች ማህበራት ጥምረት እና የተግባር ቅንጅት ጉድለት እንዲሁም በሜይንስትሪሚንግ የተቀመጠ በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ አለመዋሉ የሚስተዋሉ ጉድለቶች ናቸው፡፡

በውይይት መድረኩ በቀጣይም አፅንዖት ሊሰጥባቸው ይገባል የተባሉ ጉዳዮች ተነስተዋል በዚህም ይበልጥ ተጋላጭ ተብለው በተለዩ ማህበረሰብ ክፍሎች፣በቀን ወይንም በተንቀሳቃሽ ሠራተኞች፣ የትዳር አጋሮቻቸው የሞቱባቸው፣በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችና ደንበኞቻቸው ዘንድ የሚስተዋሉ መዘናጋቶችን እና የመሳሰሉችግሮችን በመቅረፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ወረርሽኝን ስጋት ተቀምጧል።

በመጨረሻም በኤች አይ ቪ / ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት አፈፃፀም አርአያነት ያለው ተግባር ለፈፀሙ ግለሰቦች እና ማዕበራት ፣ የድርብ አደራ መልዕክት ምስጋናና ዕውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት የምክክር መድረኩ ተጠናቋል ።