በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ

የደ/ብ/ብ/ህ /ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የ2014 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በጂንካ ከተማ መጀመሩን አስታወቀ በመርሀግብሩ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ እና የማናጅመንት አካላት በጂንካ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤት ከማደስ ባሻገር የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች የሆኑትን የችግኝ ተከላ ስራ እያከናወኑ ይገኛል። የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን ተደራሽ የሚሆኑት አቅም የሌላቸውና አቅመ ደካማ ዜጎች የመደገፍ ስራ በግል እና በቡድን በመቀናጀት በመስራት በአገራችን ያሉትን ዜጎች ችግሮች ከችግር ለማውጣት የሁላችንም ተነሳሽነት እና ርህራሄ የሚጠይቅበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል። ኃላፊው አያይዘውም በአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቸገርን ያለንበት ወቅት በመሆኑ የአርንጓዴ አሻራ በተለያዩ አካባቢዎች ችግኝ በመትከል ፣የአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት እድሳት በማጠናከር፣ ሐአገር ተረካቢ ወላጅ አጥ ህጻትት በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር እናት በደም እጦት ምክንያ እንዳትሞት የደም ልገሳ በማድረግ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ወቅት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። በ2014 በጀት በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ቢሆንም የበጎ አድራጎት ስራን ከፍ በማድረግ ረገድ የወጣቶች ሚና ወሳኝ በመሆኑ ወጣቶች እንዲበረታቱ ጤና ቢሮ የተለያዩ ግብአቶች አጠናክሮ የሚለግስ መሆኑን ገልጸዋል። የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የደ/ኦሞ ዞን አስተዳደሪ አቶ ንጋቱ ደንሳ ባስተላለፉት መልዕክት በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ነው በሚል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ የተጀመረው በአገራችን የበጎ አድራጎት ባህላችን በማጠናከር ካለን የማካፈል ተግባር ስንፈጽም የፈጣሪን ትዕዛዝ መፈጸም እና መባረክ በመሆኑ ሁላችንም ለበጎ አድራጎት ስራ መተባበር እንደሚገባ ተማጽነዋል። አስተዳዳሪው አያይዘውም በአካባቢው በመማሪያ ቁሳቁስ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እና በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ማድረግ በመቻሉ ለክልል ጤና ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል። በዚህን ጊዜ የ2015 የትምህርት ዘመን በመማሪያ ቁሳቁስ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ የመግዛት አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ለ50 ተማሪዎች በአይነት የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች የተበረከተላቸው ሲሆን ከመማሪያ ቁሳቁስ ባሻገር ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያዎች ተበርክቶላቸዋል። በዚህን ዕለት የቤት እድሳት፣ ለተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁስ የመለገስ፣ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ባሻገር የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሄዶል። በመርሀ ግብሩ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባለት፣ እና የጂንካ ዞን ከፍተኛ አመራር በተገኙበት መርሀ ግብር እየተተገበር ነው።
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ