በጋሞ ዞን ባለፉት አራት ወራት ከ14 ሺህ 900 በላይ ሕጻናት የክትባት አገልግሎት አግኝተዋል

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታዬ እንደገለፁት በዞኑ ከአንድ ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ 14ሺህ 970 ሕፃናት ሁሉንም ዓይነት የክትባት አገልግሎት ሽፋን ተከታትለው አጠናቀዋል ። ለሕፃናት ሕመምና ሞት ዋነኛ ምክንያት የሆኑትን የጤና ችግሮች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀነስ የሚሰጠው አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉን የመምሪያው ኃላፊው ተናግረዋል ። የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል ባለፉት አራት ወራት በተደረገው ቅደመ ወሊድ ክትትል 18 ሺህ 61 ጨቅላ ሕፃናት ከመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ነፃ ሆነው መወለዳቸው ተገልጿል።
ዕድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ሕፃናት የቲቢ በሽታ ፥ የ”ፔንታ ሻለንት 3″ ፥ የሳንባ ምች ፥ የተቅማጥ እና የፖሊዮ መከላከያ አንደዚሁም ከ15 እስከ 23 ወር ዕድሜ ክልል ያሉ ሕፃናት የኩፍኝ ክትባት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል ።
ምንጭ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ