በወረርሽኞች እና በድንገተኛ አደጋዎች የማይበገር የጤና ስረዐትን እውን ለማድረግ ተግባራት ቀጣይነትን እንደሚሹ ተገለፀ

በወረርሽኞች እና በድንገተኛ አደጋዎች የማይበገር የጤና ስረዐትን እውን ለማድረግ ተግባራት ቀጣይነትን እንደሚሹ ተገለፀ ለድንገተኛ አደጋ የማይበገር የጤና ስርዓት ዕውን ለማድረግ በየደረጃው ተግባራዊ ምላሽን የማረጋገጥ ስራዎች በተግባር ሊታጀቡ እንደሚገባቸው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ባካሄደው የሳምንታዊ ውይይት አስታውቌል፡፡ በዚህ የሳምንታዊ የውይይት መድረክ የወባ ስርጭት ፣በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ የህጻናት መቀንጨርና መቀጨጭ ተግዳሮቶች ፣ የኩፍኝ ፣የማጅራት ገትር በሽታ ጫና እንዲሁም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ክስተቶች ያሉበት ደረጃ ተመላክቷል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ብሎም በክልላችን እየተከሰቱ ያሉ በሽታዎችን ጫናና ወረርሽኞችን ለመከላከል የድንገተኛ አደጋ የጤና ችግሮችን በመለየት ተግባራዊ ምላሽን የማረጋገጥ ስርዓት ዕውን ለማድረግ ያለው ሚና የላቀ በመሆኑ ተግባራት በዚሁ ልክ በታችኛው መዋቅር ተይዘው ሊመሩ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ የወባ ስርጭት እንደ ክልል አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ ጭምር እየተነሳ ነው፡ በመሆኑም ስርጭቱን መከላከልና መቆጣጠር እርምጃዎች ተግባራዊነትን ማረጋገጥ በጤና በማህበራዊ ፣የኢኮኖሚው ላይ ሊከሰት የሚችለውን ጫና መቅረፍ ይገባል ነው የተባለው፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች አንዱ የክትባት ተደራሽነትን ማስፋት በመሆኑ በዚህም አንፃር ሶስተኛው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን ለማዳረስ ተግባራት በሰፊው አየተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል፡ በውይይቱ የተከናወኑ ተግባራት በንጽጽር ጭምር በትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች፣ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የጤና ተግባራትን በተመለከተ ቀርቧል ለተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽም ተሰጥቶባቸዋል ፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ