በክልሉ ጤና ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ወርሽኝ አሁናዊ የስርጭት ሁኔታ ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት የኮሮና ቫይረስ የወረርሽኝ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቶ በየቀኑ በአማካይ የ2 ሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል በመሆኑ ከመዘናጋት በመወጣት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ /መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ ጥሪ አቅርበዋል ።

ሃላፊው በመግለጫቸው የበሽታው አምጪ ቫይረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን እየቀየረ መምጣቱ በሽታውን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት እጅገ በጣም ከባድና ፈታኝ እያደረገ የሚገኝ ፤ በተለይም በቅርቡ በሀገራችን መሰራጨቱ የተረጋገጠው ‘’ዴልታ’’ የተባለው አዲሱ ዝርያ በፊት ከነበሩት ዝርያዎች 70 በመቶ የበለጠ የመሰራጨት አቅም ያለውና የበለጠ ገዳይ መሆኑ አሁን እየታየ ካለው የህብረተሰቡ መዘነጋት ጋር ተዳምሮ ከፊታችን አስፈሪ አደጋ መደቀኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለውታል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የቫይረሱ ሁኔታ የዛሬውን ሪፖርት ሳይጨምር እስከ ትላንትናው ድረስ በክልላችን 11,890 ሰዎች በበሸታው የተያዙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 181 ታካሚዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የሞት መጣኔውን ስናይ 1.5 በመቶ ሲሆን ይህም ማለት ከ100 ታካሚዎች ሁለት ስዎችን እየገደለ ይገኛል ማለት ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ1,100 በላይ የሚሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን ሰላሳ ሰባቱ (37) በጠና የታመሙና ኦክስጂን የሚያስፈልጋቸው፣ አስራ ስድስቱ (16) በጽኑ ታመው የሰው ሰራሽ ማሽን እገዛ የሚፈስልጋቸው ከዚህም ውስጥ አስሮቹ (10) ታማሚዎች የሰው ሰራሽ ማሽን ላይ ሲሆኑ ስድስቱ (6) ደግሞ ማሽን በመጠባባቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ እስከ ትላንትናው ያለዉን የዚህን ሳምንት የበሽታውን ስርጭት ሁኔታ ስናይ 1,205 ሰዎች በብሽታው የተያዙ ሲሆን በአማካይ በበሽታው የመያዝ ምጣኔም እያሻቀበ መጥቶ 25 በመቶኛ ደርሷል፡፡

ይህም ማለት ከተመረመሩት 100 ሰዎች ውስጥ ሀያ አምስቶቹ (25) ላይ በሽታው እየተገኘ መሆኑነ ያሳያል፡፡ እንዲሁም በሳምንቱ ውስጥ በሽታው የ14 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

የዚህን ሳምንት የበሽታውን ስርጭት ካለፉት ሳምንታት ጋር ስናነጻጽር የዛሬን ሳይጨምር በዚህ ሳምንት በበሽታው የተያዙ ሳዎች ቁጥር ከባለፈው ሳምንት በ271 ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከ2 ሳምንት በፊት ከነበረው ጋር ስናነጻጽር ደግሞ በ3 እጥፍ ጨምሯል፡፡

በበሽታው የመያዝ ምጣኔንም ስናይ የዚህ ሳምንት ካለፈው ሳምንት በ25 በመቶ የጨመረ ሲሆን ከ2 ሳምንት በፊት ከነበረው ጋር ስናስተያይ ደግሞ የ40 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ አሳሳቢ መሆኑን አመላክተዋል ።

በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት ካለፈው ሳምንት በ75 በመቶ እንዲሁም ከ2 ሳምንት በፊት ከነበረው ጋር ስናስተያይ ከ3 እጥፍ በላይ ጨምሯል፡፡

ከላይ የጠቀስናችው አሃዛዊ መረጃዎች የሚያሳዩት በሽታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እይተባባሰ መምጣቱንና ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሰምቶ ተግባራዊ ካላደረገና የበሽታውን ስርጭት መግታት ካልተቻለ ከአቅም በላይ ወደ ሆነ ሁኔታ እያመራን መሆኑን ያሳያል ብለውታል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን ፤እጆችን በመታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣በመከተብ ቫይረሱን መከላከል አማራጭ የሌለው ተግባር ተደርጎ ለወሰድ ሊወሰድ ይገባዋል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።