በክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

የጤና ቢሮ ሃላፊ በሀገራችን እንዲሁም በክልላችን በአብዛኞቹ አከባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን ለማለት እፈልጋልሁ በማለት በዓሉን ስናከብር በሀገራችንም ሆነ በክልላችን በክፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውንና ለብዙዎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት እየሆነ ያለው የኮሮና በሽታ የመካላከያ ጥንቃቄዎችን በፍጹም መዘንጋት የለብንም ብለዋል ።

የወረርሽኙ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቶ በየቀኑ በክልሉ በአማካይ የ2 ሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል የዛሬን ሪፖርት ሳይጨምር እስከ ትላንትናው ድረስ በክልላችን 11,890 ሰዎች በበሸታው የተያዙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 181 ታካሚዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል።

የዚህን ሳምንት የበሽታውን ስርጭት ካለፉት ሳምንታት ጋር ስናነጻጸር የዛሬን ሳይጨምር በዚህ ሳምንት በበሽታው የተያዙ ሳዎች ቁጥር ከባለፈው ሳምንት በ271 ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከ2 ሳምንት በፊት ከነበረው ጋር ስናነጻጸር ደግሞ በ3 እጥፍ ጨምሯል ብለዋል።

ከዚህም የስርጭት መጠን መጨመር ጋር በተያያዘ በየሆስፒታሎቻችን ከፍታኛ የሆነ ታካሚዎች አልጋ፤የሰው ሰራሽ መተንፈሻ ማሽንና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመን መሆኑን ተገዝበን የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ማለትም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በአግባቡ መጠቀም፣ ርቀትን መጠበቅ፣ እጆቻችንን በውሀ እና በሳሙና/ሳኒታይዘር ማፅዳት፣ ሰዎች በሚበዙበት ቦታ ባለመሰባሰብ እንዲሁም ክትባቱን መከተብ በተጨማሪም ተሻሽሎ የወጣውን መመርያ ቁጥር 803/2013ን ተግባራዊ ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል።

በመጨረሻም እንደ መስቀል ባሉ ህዝባዊ በዓላት ወቅት እያንዳንዱ ግለሰብ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የጸጥታና ፍትህ አካላት ና ሌሎቸ ባለድርሻ አካላት የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው ሀላፍነታቸውን እንዲወጡ ጥርዬን አስተላልፋለሁ በማለት መልካም በዓል መልዕት አስተላልፈዋል ።