በክልሉ ጤና ቢሮ ሁሉ አቀፍ የህክምና ተሃድሶ እና የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎቶች ሽግግር የመግባቢያ ሰነድ ላይ ውይይት አደረገ

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ሁሉ አቀፍ የተሃድሶ ህክምና እና የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎቶች ሽግግር የመግባቢያ ሰነድ ላይ ውይይት አደረገ

ስምምነቱ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስትጤና ቢሮ እና በክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መካከል የአርባምንጭ አካላዊ ተሃድሶ ማዕከል ተግባርና ኃላፊነት ሽግግር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ እና ታውቋል፡፡

በቀጣይም እስከሁን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር በጥቅል ተይዘዉ ከነበሩ የአካላዊና ማህበራዊ ተሃድሶ ተግባርና ሃላፊነቶች ወደ ጤና ቢሮ ይሸጋገራሉ ተብሏል፡፡

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የጤና አገልግሎት ግቦች ተግባራዊነት ሲነሳ ህክምናና ተሃድሶ ተግባር ተጠቃሽ መሆኑ በተለይም መከላከልን መሰረት ባደረገው የጤና ፖሊሲ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አውስተዋል፡፡

የውይይቱ ዋነኛ አላማ የአካላዊ ተሃድሶ ስራዎችንና ኃላፊነቶችን ወደ ጤና ቢሮ ለማሸጋገር በሚያስችል ስምምነት ላይ የጋራ አቋምና ግንዛቤ ለመያዝ ታላሚ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በህክምና አገልግሎቶች የስፔሻሊት ሰርቪስና የተሃድሶ ህክምና ፎካል አቶ ደረሰ ደሳለኝ በበኩላቸው የመሸጋገሪያ ስምምነቱ ሁለቱ ቢሮዎች በቀጣይ የአካል ጉዳተኞችን ህይወት ለማሻሻል በሚሰሩ ሁሉ አቀፍ የተሃድሶ ህክምና እና የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎቶች ላይ የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላት የመምራት የማስተባበር ስራዎች ዉጤታማ በሆነ አግባብ እንዲፈፀሙ ተደጋግፈዉ ለመስራት የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በቀጣይም የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎቶችን በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች፣ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች እንዲስፋፉ የማድረግ ተግባራት ባለድርሻ አካላትን መንስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ባሳተፈ መልኩ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የማኔጅንት አባላት በትግበራ ወቅት ከሰው ሃይል፣ ከጤና ቁሳቁስ አቅርቦት አያያዝ ፣ከበጀት አጠቃቀም እንዲሁም በቀጣይ ተግባራትን በጋራ በማከናወን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል፡፡

የስምምነት ሰነዱም በቀጣይ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማካተት በድጋሚ ለውይይት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡