በኤች አይቪ ኤድስ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተደረገ

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃለፊና ዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስን የመከ/የመቆጣጠር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ባስተላለፉት መልእክት የመድረኩ ዓላማ የኤች አይ ቪ ምርመራና የህክምና አገልግሎቱን ማጠናከር እንደሆነ ገልጸው ከ1998-2002 ዓ.ም ድረስ የነበረው ኤች አይ ቪ የመከላከልና መቆጣጠር እና የማህበረሰብ ንቅናቄ በፈጠረው መነቃቃት በክልላችን የኤች አይ ቪ ስርጭት እንዲቀንስ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በማሰብ አሁንም ሁሉም ባከድርሻ አካላት እንደ ሀገር በ2030 የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በህክምና ላይ ያሉ ህሙማን መድሀኒታቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ ከማድረግ አንጻር በክልላችን መጠነ ሰፊ የሆነውን የመድሃኒት ማቋረጥ ችግር አሳሳቢ በመሆኑ የሚዲያ አካት የበኩላቸውን እንዲወጡ እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ በማፍራት ረገድ የኃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

መሠረታዊ የኤች አይቪ ኤድስ እውነታዎች ምን ምን እነደሆኑ የሚገልጽ መረጃ ሰነድ በዶ/ር አብርሃም የቀረበ ሲሆን በዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ የመከ/የመቆጣጠር ዋና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ጸሀይ አሰፋ ባከፉት ሶስት አመታት ኤች አይ ቪን በመከላከል ረገድ በኃይማኖት ተቋማት፣ በሚዲያዎች እንዲሁም ቫየረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ማህበራት ያበረከቱትን አስተዋጸኦ እና የመጡ ለውጦችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በቀጣይም በእምነት ላይ የተመሰረተ የፀረ ኤች አይ ቪ አገልግሎቶች ላይ መቆየትና የመድሃኒት ቁርኝቱን እንደሚገባ ተገልጸዋል።
በቀረቡ ጽሁፎች ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስቶ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ የመከ/የመቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ትላንት በጋራ ርብርብ ሰርተን ያመጣናቸውን ለውጦችን በማሰብ አሁን በተቀናጀ መንገድ ብንረባረብ ከሚጠበቀው ውጤት በላይ ማምጣት እንደምንችል ያሳያል ብለው በሁሉም አካባቢዎች የተቀዛቀዘውን የኤች አይ ቪ ጉዳይ ሁላችንም የየራሳችንን ድርሻ በመውሰድ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት ወቅታዊ መረጃዎች፣ ታዓማኒነታቸው ከተረጋገጠ የመረጃ ምንጭ በመውሰድ መረጃዎችን በወቀቱ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ወጣቶችን ከኤች አይ ቪ መከላከል ይገባል በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው እለት በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ በተደረገው የምክክር መድረክ የኃይማኖት አባቶች፣ የሚዲያ ኣካላት፣ ቁልፍ ሴክተር መ/ቤቶች እንዲሁም ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ማህበራት ኃላፊዎች ተወካዮች ተሳታፊ እንደሆኑም ተጠቁሟል።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ