በኤችአይቪ እንዲሁም ቲቢ ልየታና ህክምና በሚፈለገው ልክ ውጤት አልመጣም

በቲቢ እና ኤች አይ ቪ ምርመራ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን በመግለፅ ምርመራው ተጋላጭ ተኮር አለመሆን በዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት በተግዳሮትነት እንደጠቀስ ይህንንም ለማሻሻል እና እብረተሰቡን ከነዚህ አስከፊ በሽታዎች ለመታደግ ተግባራት በንቅናቄው ማስኬድ ማስፈለጉን የተናገሩት የ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በቀጣይም በርካታ ስራዎች ልንሰራ ይገባናል ብለዋል።
ሃላፊው በንግግራቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክስተት በጤና ተቋማት የቲቢ/ ኤች አይ ቪ የክትትል ስራ እንዲሁም የመድሃኒት ተጠቃሚዎች ምልልስን ጭምር አሳሳቢ እንደሚያደርገው ገልፀው ህብረተሰብ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጨምሮ ከነዚህ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ሌሎችን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የዘርፈብዙ ኤች አይቪ /ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው በኤች አይ ቪ /ቲቢ ያለባቸው ሰዎች ልየታና ህክምና ማስጀመር ንቅናቄ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦችን አንስተዋል ንቅናቄውን የተሳካ ለማድረግ የጋራ ርብርብ ፣የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ሚና ለግቡ ስኬት ተጠባቂ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
በዚሁ ወቅት ከውይይቱ ተሳታፊዎች አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት በየጊዜው በሚከናወኑ ተግባራት በቲቢ ኤች አይቪ ልየታ የሚቀመጡ የግብ ስኬትችን ማረጋገጥ አለመቻሉ የሚገለፀው ከሰዉ ልጆች ጤና በመሆኑ በንቅናቄው እነዚህን ክፍቶች ለማረም አላፊነት እንደሚወስዱ በእንችላለን ተግባራት ለስኬታማነቱ እንደሚጥሩ ተናግረዋል ።
በመሆኑም አፈፃፀም ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመድሃኒት አቅርቦትና መቆራረጥ ፣የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራትን ማጠናከር ፣እንዲሁም መረጃ የማደራጀት በተገቢው የመጠቀም ተግባራት ከተለመደው አካሄድ ተላቆ ውጤት አምጪ አፈፃፀሞች ከወዲሁ ሊታሰብባቸው እንደሚገባ አመላክተዋል ።
የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት ጤና ቢሮ