በሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት በአገርአቀፍ እና በክልል ክፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡና ተሸላሚ ለነበሩ ሆስፒታሎች የእውቅና እና የሽልማት ተካሂዷል

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የ2013 በጀት ዓመታዊ ጉባዔ ላይ እውቅናና ሽልማት በሰጠበት ወቅት ለሽልማቱ መነሻ የሆነው የጤና ተቋማትን ፅዱና ምቹ በማድረግ፣ ወቅቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት በመስጠት፣ ተቋማዊ ለዉጥ በማምጣት በሀገርአቀፍም በክልልም ደረጃ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው የተመረጡ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በሀገርአቀፍ ደረጃም ሻምፒዮን የሆነውና በክልላችንም የላቀ የጤና ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ለሆነው የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጭምሮ፣ ንግስት ኢሌኒ መታሰቢያ ኮምረኸንሲቭ ሰፔሽየላይዝድ ሆስፒታል፣ ቦንጋ ገብረጻዲቅ ሻዎ ጀነራል ሆስፒታል እያንዳንዳቸው ሶስት ሚሊዮን ከጤና ሚኒስቴር የተሸለሙት የአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆስፒታሎች በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮም ለእያንዳንዳቸው 750 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በአገራቀፍ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊዮን ተሸላሚ የነበሩት ቡታጅራ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ጂንካ ጠቅላላ ሆስፒታል እና አርባምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ደግሞ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮም ለእያንዳንዳቸው ለላቀ አፈጻጸማቸው የዋንጫና የ500 ሺህ ብር ተሸላሚዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በእውቅናና በሽልማት መርሃ ግብሩ የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ በተመሳሳይም ዶክተር ቦጋለች ገብሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የ300 ሺህ ብር እና የሰርተፊኬት እንደተበረከተላቸው እና በጤናው ሴክተር የላቀ የህይወት ዘመን አገልግሎት ያላቸው ፣በሙያቸው የላቀ እና የአመራርነት ሚናቸው በልቀት የተወጡ ግለሰቦች ጭምር ሽልማት መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡