የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተስብ ጤና ኢንስቶቲዩት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ በወላይታ ሶዶ እያካሄዷል የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ተፈጥራዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ተከተሎ ያጋጠሙ ነባርና አዳዲስ ወረርሽኞች እንዲሁም የእናቶች ህፃናት ሞትን ለመቀልበስ የአሰራር ማሻሻዮች፣የአደጋ መከላከል ትንበያ ቅድመ ዝግጅት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አሰራሮችን ማጠናከር ይገባል:: የዜጎችን የኑሮና የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ወቅቱን የሚዳስሱ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎች ላይ አስፈላጊ ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ አሰራሮችን መዝርጋት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ገለፀዋል:: ኢንስቲቲዩቱ በክልሉ የሚገኙ የምርመራ ላብራቶሪዎች አለም አቀፍ ስታንዳርድ የጠበቁ መሆናቸውን በመቆጣጠር የእውቅና እና የጥራት ማሻሻያ እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኖንም አመላክተዋል። በየወቅቱ የሚፈጠሩ ችግሮችንም ለመለየት አስፈላጊና ተግባራዊ ድጋፍ በሚሹ ርዕሰ ጉዳዮች ጉዳዮች ላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ መፍትሄ የማመላከት ስራም በመሰራት ላይ መሆኑንም ገልፀዋል:: የሰው ኃይልና ለጤና ተቋማት የህክምና መገልገያና ማቋቋሚያ የሚውል ግብአት እጥረት፣ የመረጃ ቋት አስተዳድርና ትንተና አለመዳበር በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙ ችግሮች መሆኑን ጠቁመው ይህንንም ለማሻሻ የሰለጠነና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል እንዲኖር በስልጠና ማገዝ፣ የበጀት ማሻሻያ እና መረጃ ቋትን አያያዝን ማዘመን ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል:: በ2014 የስራ ዘመን ያልተጠናቀቁ ተግባራት ላይ በማተኮር የኢንስቲትዩቱ የስራ አፈጻጸም ስኬት እና ክፍተት በመለየት ሰራተኛው የበኩሉን መወጣት እንደሚጠበቅበት ዳይሬክተሩ አሳስበዋል::
የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን!