ምግብና ስርዓተ ምግብን ማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተሰራባቸው መሆኑ ተገልጿል

በጤናው ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ታላሚ ያደረገ የዘርፈ ብዙ የስርዓተ ምግብ ተግባራት ውይይት ተካሂዷል ።

የውይይት መድረኩን የደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ/ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አመካሪ አቶ ፀደቀ ሱገቦ እንዲሁም የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሃላፊ አቶ መና መኩሪያ በጋራ መርተውታል መልዕክትም አስተላልፈዋል በምግብና በስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን ተግባራዊነት ማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት በዘርፍ ያግዛል።

ይህንንም ለማረጋገጥ ለስርዓተ ምግብ ተጋላጭ የሆኑ አከባቢዎችን እና የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም በወጣት ሴቶች ፣በነፍሰ ጡር እናቶች፣ ጡት በሚጠቡ እና በተለይም አምስት ዓመት በታች ዓመት እድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ሕፃናት ላይ ተገቢዉን ትኩረት ሰጥቶ ተግባራት ቢከናወኑም የሚፈለገውን ውጤት መጥቷል ብሎ መውሰድ አዳጋች መሆኑ ተመልክቷል ።

በአካልም በአህምሮ የዳበረና የበለፀገ ትዉልድ እንዲፈጠር ምግብና ስርዓተ ምግብን ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማጠናከር ፣የማስፈፀም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ አስብ አስተያየቶች ተሰጥተውባቸዋል።

በዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ፣ ከመዋቅር ጋር በተያይዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ ፣የአመራሩን የመሪነት ሚና ማጎልበት፣ ፣የግንዛቤ ማስጨበጨ ስራዎችን አጠናክሮ መፈፀም እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመጨረሻም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ፣ የክልሉ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ቢሮዎችና የስራ ሃላፊዎች ፣ከፍተኛ ሃላፊዎች የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች ተሳታፊ በሆኑበት በዘርፈ ብዙ ስርዓት ምግብ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበዋል።

የደ/ብ/ብ/ሕ/ ክ/መንግስት ጤና ቢሮ