ማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህንን እንዲሁም ኮቪድ 19 (የኮሮና ቫይረስ) መከላከል በተመለከተ የቅስቀሳ ስራ መሰራቱ ተገለጸ

ይኸው የመከላከል ተግባር በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ፣ ሀደሮ ከተማ ገበያ ላይ እንዲሁም ዱራሜ ከተማ ገበያ ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው መሰራቱም ታውቋል።

በእነዚህ አካባቢዎች የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ በመሆን በራሱ እና በቤተሰቡ ላይ በድንገት ከሚደርስ የጤና እክል አፋጣኝ መፍትሔ ለማግኘት ለነገ ብሎ የቆጠበውን ሀብትና ጥሪት በድንገት አባክኖ ወይም አስይዞ ከመታከም ይልቅ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን አባል በመሆን በዓመት አንድ ጊዜ ጥቂት ገንዘብ ከፍሎ የራሱንና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ እንደሚቻል ተገልጾ በከምባትኛ ቋንቋ የቅስቀሳ ስራ የተሰራ ተሠርቷል።

አስከ ጥር 30/2013 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ ተመዝጋቢም ሆነ አሮጌ የአባልነት ካርድ የሚያሳድሱ የህብረተሰብ ከፍሎች በየቀበሌያቸው በአካል በመቅረብ መመዝገብና ካርዳቸውን ማሳዳስ እንዳለባቸው በቅስቀሳው ላይ ተመላክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶቹን በመግለጽ በከምባትኛ ቋንቋ የንቅናቄ ስራ የተሰራ ቢሆንም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚስተዋለው ከፍተኛ መዘናጋት በህዝባችን ላይ ቀውስ እንዳያስከትል ልዩ ትኩረት በመስጠት የመከላከሉን ስራ ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።