መረጃን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለመዘርጋት…

የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ የ2014 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 ዓ.ም እቅድ ውይይት እንዲሁም የIPC ይፋዊ የማስጀመሪያ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። በዚሁ ጊዜ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ሽፈራው መረጃን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተሻሻለ እና ያልተቆራረጠ የጤና አገልግሎት ተግባር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር አገልግሎትን በማሻሻል: የቀዶ ህክምና አገልግሎትን በማሻሻል; የጨቅላ ህጻናት ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሌሎች መሠል ተግባራትን ማጠናከር የማህበረሠቡን የጤና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አቶ ቢኒያም ገልጸዋል። በዚሁ ወቅት በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን በየጤና ተቋማቱ ያሉ የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ከተቀረፈና ተቋማት በየዕለቱ የሚሰሩትን የቀዶ ህክምና ቁጥር ካላቸው የሰው ሀይል ጋር አጣጥሞ የመስራት ልምድ በማስፋት በዘርፉ ከሚነሱ የመልካም አስተዳደርና እሮሮ መሻገር እንደሚቻል ተመላክቷል። በጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ሰፊ ቁጥር ያለው ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲያገኝ ቀማድረግ ረገድ አገልግሎቱን በተሻለ ጥራት መስጠት የሚያስችል የጤና ጣቢያ ሪፎርም በአስር ምዕራፎች በተከፋፈሉ ስታንዳርዶች እየተሰራ ቢሆንም የአገልግሎት ማነቆዎችን መፍታት የሚያስችል revised EHCRIG በ12 ምዕራፎች እና በ131 መተግበሪያ ስታንዳርዶች ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱም ተገልጿል። በሁሉም አከባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ ለታካሚዎች ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል PHCG ትግበራም መጀመሩም ተመላክቷል፡፡ በመጨረሻም በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ የተሠጠ ሲሆን የተገኙ መልካም ተምክሮዎችን በማስፋት ላጋጠሙ ተግዳሮቶች የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት ውይይቱ ተጠናቋል።
የደ/ብ/ብ/ሕ /ክ /መንግስት ጤና ቢሮ