ለህጻናት ሁለንተናዊ እድገት የጎላ ሚና ያለው የጡት ማጥባት ልምድ ሊጎለብት ይገባል

ጡት ማጥባት ምንጊዜም ይቅር የማይባል ህጻናቱን በጤንነትና በደህንነት ለማሳደግ የእናቶችና የመላው ህብረተ ሰብ ኃላፊነት በመሆኑይህንን የሚያስገነዝብ የጡት ማጥባት ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ግዜ ተከብሯል፡፡ በክልል ዓቀፍ ደረጃ በስልጤ ዞን በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ እና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ በመልዕክታቸው የእናቱን ጡት ወተት ለህጻናት ሁለንተናዊ እድገት ልጆች በጤናማነት እንዲኖሩ የሚያደርግ ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ጥቅሙ ለቤተሰብም ፣ለማህበረሰብም ፣እንደ ሀገርና እንደ ዓለም በመሆኑ እናት ልጅዋን ከወለደችበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ካለም ንም ድብልቅ የጡት ወተቷን ብቻ እንድትሰጥ ለማበረታታት የጋራ አላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሺፋ በበኩላቸው ለትውልድ የሚሰራ የእናት ጡት ወተት ለህጻኑ መስጠት የልጁንም ሆነ የእናትየውን ጤንነት በመጠበቅ ህጻኑ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ ያስችለዋ ለዚህም እናቶች ጡት ማጥባቱን ለመጀመርም ሆነ ሳያቋርጡ ለመቀጠል ድጋፍ ሊያገኙ ይገባቸዋል ብለዋል በዚህ ደረጃ ለሆስፒታሉ ለሚሰሩ እናቶች ከስራ ገበታቸው ሳይነጠሉ በተገቢው ልጎቻቸውን ማጥባት እንዲችሉ የህጻናት ማቆያ መዘጋጀቱንና አገልግሎት እየሠጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ጡት ማጥባት ልምድ ለማሳደግና ለማበረታታት እንዲሁም አስፈላጊ መሆኑን በጽኑ ለማሳየት በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንዲሁም በስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የህጻናት ማቆያ መዘጋጀቱንና ለዚህም ለሌሎች አከባቢዎች ጭምር በምርጥ ተሞክሮነት ሊስፋፋና ለሌሎችም ማስተማሪያ ሊሆን ይገባዋል በማለት የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ እውቅናና ሰርተፍኬት ሰጥቷቸዋል፡፡